album cover
Belay
7.283
World
Belay wurde am 10. September 2002 von Maebel Production als Teil des Albums veröffentlichtAmen
album cover
AlbumAmen
Veröffentlichungsdatum10. September 2002
LabelMaebel Production
Melodizität
Akustizität
Valence
Tanzbarkeit
Energie
BPM148

Credits

PERFORMING ARTISTS
Neway Debebe
Neway Debebe
Vocals
COMPOSITION & LYRICS
Neway Debebe
Neway Debebe
Songwriter
PRODUCTION & ENGINEERING
Abegasu Shiota
Abegasu Shiota
Mixing Engineer

Songtexte

ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ
ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ
ሰንዝሮ ማይመልስ ወርዶ ማይረታ
በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ
እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና
የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና
ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወድያ ማዶ
የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ (አቤት)
ልክ እንደ ጀግና ሰው ምነኛ በረታው (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ምነኛ በረታው ምነኛ በረታው
ጎጃም ተሻግሬ ጎብዝ ሆኜ መጣው (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ጀግና ሆኜ መጣው አንቺን ይዜ መጣው
እንግዲያው ያውልሽ ውሰጂኝ ማርኪና (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ውሰጂኝ ማርኪና ውሰጂኝ ማርኪና
እንደፈለክሽ አርጊኝ የበላይ ነሽና (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
የበላይ ነሽ እና የጎበዝ ነሽና
ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ
አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማሬዋ
ጋምዬ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ
ደፋር አርጊው ልቤን እንደ በላይዬ
ጋምዬ
ጋሜዋ
ወይ ደምዬ
ውይ ደሜዋ
እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
እውይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
ሁል ጊዜ ከፍ ብለሽ የምትቀጪ
የበላይ ሆነሽ ነው የምትመረጪ
በላይ የመረቀው ሀገሩን ነው መሰል
ቢወለድ ጀግና ሰው የሚይስጠራ በድል
የበላይ ፀባይ ይዘዋል ሰዎቹም
ለፍቅር ነው እንጂ ለፀብ አይመቹም
ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ
ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ
ሰንዝሮ ማይመልስ ወርዶ ማይረታ
በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ
እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና
የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና
ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወድያ ማዶ
የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ
ዙሪያ ዳር ድንበሩን አፈሩን ኩሩበት (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ሀገሩን ኩሩበት እንድትመኩበት
እነ በላይ ናቸው የተወለዱበት (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
የተፈጠሩበት ታሪክ የሰሩበት
ከእንግዲ ጎጃም ላይ ምን ተሰራ አትበሉ (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ምን ተሰራ አትበሉ ምን ተሰራ አትበሉ
ታሪክ ጠይቃችው በላይ በላይ በሉ (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ)
ጀግናው በላይ በሉ ጎበዝ ወዳድ ሁሉ
ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ
አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማሬዋ
ጋምዬ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ
ደፋር አርጊው ልቤን እንደ በላይዬ
ጋምዬ
ጋሜዋ
ጋምዬ
ጋሜዋ
እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
እሰይ ስበቤዋ እሰይ ድማሜዋ
ሀይማኖተ ፅኑ ልበ ኩሩ ነሽ
ከእነ በላይ ሀገር ጎጃም ተወልደሽ
ኧረርዬ ርዬ ኧረርዬው መላ
ጎጃም ተገበየ ፍቅር እና ተድላ
እኚህ ጎጃሜዎች ልዩ ጣዕም አላቸው
የንቦች እንጀራ ማር እያበሏቸው (አቤት ምቺና)
(አቤት ምቺና)
(አቤት ምቺና)
Written by: Neway Debebe
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...