Credits

Lyrics

የፍቅር ሎንችና ሆነ ወይ አታላይ
የመውደድ መንገዱ ሆነ እንዴ አታላይ
ተነጥፌ እንደ ጨርቅ ለዘወትር ስታይ
እንዲያው ምቹ ሆኜ ፊት ለፊት ስታይ
ወደድኩሽ ወደድኩሽ በዛ እንዴ ቀን በቀን
አይን አይንሽን ማየት በዛ ወይ ቀን በቀን
ምነው ታዲያ ሳቅሽ አያሌ ናፈቀን
የፊቱ ጨዋታሽ እጅጉን ናፈቀን
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
ያቃዠኛል መሰል ክፉኛ ይህን ሰሞን
ነገርኩ እንዲያሰነሱኝ ከቅዝት ይህን ሰሞን
ከእንቅልፌ ስነቃ አገኝሽ እንደሆን
ሰመመኑ ሲያልፍ ትመጪ እንደሆን
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
ሳይጎድል ጎተራ ሳያንዣብ አሞራ
ተራ በተራ የገባነውን ቃል እናስብ አደራ
ሳይጎድል ጎተራ ሳያንዣብ አሞራ
ተራ በተራ የገባነውን ቃል እናስብ አደራ
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
(ምንድን ነው) ጉም ጉም በባዶ
(ምንድን ነው) ፍቅር ላይ በረዶ
(ምንድን ነው) ማልቀስ ራስ ተኩሶ
(ወዴት ነው) አፍርሶ ምሰሶ
ምንድን ነው
ምንድን ነው
ምንድን ነው
ወዴት ነው
ምንድን ነው
ምንድን ነው
ምንድን ነው
ወዴት ነው
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...