Top Songs By Zeritu Kebede
Credits
PERFORMING ARTISTS
Zeritu Kebede
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Zeritu Kebede
Songwriter
Lyrics
ውደደኝ ተብሎ ሰው አይገደድም
እውነታው ይነዳል ግን አያስገርምም
አይወደኝም
ወደውን ሳንወድ እኛም እንውቃለን
ዛሬ በተራችን እንማቅቃለን
አይወደኝም
እልቡ ውስጥ ቢኖር የፍቅር ስሜቱ
አይልም አልወድሽም በገዛ አንደበቱ
ልፋቴ ይገርማል እሱን ለማሳመን
ልቤ እያወቀ መቼም እንደማይሆን
አይወደኝም
አይወደኝም
ውደደኝ ተብሎ ሰው አይገደድም
እውነታው ይነዳል ግን አያስገርምም
አይወደኝም
ወደውን ሳንወድ እኛም እንውቃለን
ዛሬ በተራችን እንማቅቃለን
አይወደኝም
ለወደደኝ በሆንኩ ለሱ እንደምሆነው
ላይረዳኝ ነገር ጣ'ሜ ላይታየው
እሱን የሚያስጠላኝ የለም ወንድ አውቃለሁ
እንዲሁ ወድጄው ቆሜ እቀራለሁ
አይወደኝም
አይወደኝም
ተው ውደደኝ ብዬ አልጨቀጭቀውም
ልቡ ለሱ ያውቃል አላስገድደውም
የኔን አይነት ስሜት ቢኖረው ነበር ደግ
ግን በግድ አያምርም አይሆንም ሳይፈልግ
አሃ! አሃ! አይወደኝም
አሃ! አሃ! አይወደኝም
ለሌላ ሰው ፍቅር ልቤ አይከፈትም
እጎዳለሁ እንጂ ለማንም አልጠቅምም
ሰው ቀርቦ ለማቁሰል ምን አንቀዠቀዠኝ
ፍቅር ለኔ እሱ ነው እሱም አልወደደኝ
አይወደኝም
አይወደኝም
ውደደኝ ተብሎ ሰው አይገደድም
እውነታው ይነዳል ግን አያስገርምም
አይወደኝም
ወደውን ሳንወድ እኛም እንውቃለን
ዛሬ በተራችን እንማቅቃለን
አይወደኝም
Written by: Zeritu Kebede