Lyrics

እኔ የሸገር ልጅ
አንተ ከቦረና
ለፍቅር ሰጠን እጅ
ህልማችን ተሳካ
ስታወራኝ ያኔ
ለዛ ባለው ቋንቋ
ምንም ባላውቀውም
ውስጤ ግን ተረዳህ
ልቤ ከልብህ
አንዴ ቶቆራኝታ
አንተን አንተን አለች
አልሆን አላት ሌላ
ልቤ በልብህ
ታምና ተደስታ
አንተን አንተን አለች
ሆነ ምርጫዋ
መጣው ሰው ጠይቄ
Sin jaalladha ብዬ
ፍቅሬን ልገልፅልህ
ሞከርኩ ተኮላትፌ
አንተም ፈገግ እያልክ
ሙከራዬ ገብቶህ
ሲን ጃለዴ ብለህ
መለስክልኝ በቶሎ
ልቤ ከልብህ
አንዴ ቶቆራኝታ
አንተን አንተን አለች
አልሆን አላት ሌላ
ልቤ በልብህ
ታምና ተደስታ
አንተን አንተን አለች
ሆነ ምርጫዋ
አንዴ ከወደዱ
ለካ ምንም አይል ቅር
ያንተ እና የኔ ቤት
የሞላው በፍቅር
አንተም እኔን ብለህ
እኔም ላንተ ሳድር
መተሳሰብ ብቻ
የለብን ክርክር
ልቤ ከልብህ
አንዴ ቶቆራኝታ
አንተን አንተን አለች
አልሆን አላት ሌላ
ልቤ በልብህ
ታምና ተደስታ
አንተን አንተን አለች
ሆነ ምርጫዋ
ልቤ ከልብህ
አንዴ ቶቆራኝታ
አንተን አንተን አለች
አልሆን አላት ሌላ
ልቤ በልብህ
ታምና ተደስታ
አንተን አንተን አለች
ሆነ ምርጫዋ
Written by: Yamlu Mola
instagramSharePathic_arrow_out