歌词
ሕብር ተሞልቶ የነገሠን በታሪክ ማማ ላይ
መለስ ብዬ ሳልጎበኘው ማንነቴን ሳላይ
ለሃገሬ ሰው ባይተዋር ለታሪኬ እንግዳ
በኖርኩበት ባደግኩበት የኔ ባልኩት ጓዳ
እንደራሱ መሆን ያልቻለ መሠረቱን ያጣ
በሰው ክብር ልክበር የሚል ከሩቁ በመጣ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
መደማመጥ ጠፍቶት ሁሉም በራስ ወሬ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
ታላቅ እንደነበርን እንዴት ልየው ዞሬ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
ትልቅ በሆነበት ትንሽ ነኝ ሰው ካለ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
ጻዲቅ አይባልም እውነት ስለጣለ
ኧረ ናናዬ ናናዬ ኧረ ማማዬ ማማዬ
የሰም እና ወርቅ ምድር ነሽ ለካ አላውቅሽም ኢትዮጵያዬ
ኧረ ናናዬ ናናዬ ኧረ ማማዬ ማማዬ
የሰም እና ወርቅ ምድር ነሽ ለካ አላውቅሽም ኢትዮጵያዬ
ግእዝን ብታውቀው ገዳን ብታጠና
ለታላቁ ምስል ልቦናህ ቢቀና
ካለፈው መማሪያ ካልጠፋባት ሃገር
ድምሩ ባዶ ነው ከባዶ መጀመር
በል ሁን እንደሃገርህ ልሁን እንደሃገሬ
በተውሶ ዛፍ ላይ ላታፈራ ፍሬ
ላታፈራ ፍሬ
ኧረ እንደምን አለሽ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
ሕብር ተሞልቶ የነገሠን በታሪክ ማማ ላይ
መለስ ብዬ ሳልጎበኘው ማንነቴን ሳላይ
ለሃገሬ ሰው ባይተዋር ለታሪኬ እንግዳ
በኖርኩበት ባደግኩበት የኔ ባልኩት ጓዳ
እንደራሱ መሆን ያልቻለ መሠረቱን ያጣ
በሰው ክብር ልክበር የሚል ከሩቁ በመጣ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
አጥብቀው ካልያዙት ታሪክም ይጠፋል
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
የለመዱት ውሸት ከእውነት ይገዝፋል
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
ግን በእውቀት ትውልድን ካላስተሳሰረ
(ኧረ እናናዬ እናናዬ)
ታሪክ አለኝ ብቻ ምን ነገር ቀየረ
ኧረ ናናዬ ናናዬ ኧረ ማማዬ ማማዬ
የሰም እና ወርቅ ምድር ነሽ ለካ አላውቅሽም ኢትዮጵያዬ
ኧረ ናናዬ ናናዬ ኧረ ማማዬ ማማዬ
የሰም እና ወርቅ ምድር ነሽ ለካ አላውቅሽም ኢትዮጵያዬ
ከግዮን ወንዝ ዙሪያ ከኩሽ ሰፊ ምድር
ብትሄድ እስከ ፌርፌ እንደ ዑመር ሰመተር
ኢትዮጵያዊ ቀለም ኢትዮጵያዊ አሻራ
ታገኛለህ ቆሞ እውነት እያበራ
በል ሂድ ወደ ሃገርህ ልሁን እንደሃገሬ
በተውሶ ዛፍ ላይ ላታፈራ ፍሬ
ላታፈራ ፍሬ
ኧረ እንደምን አለሽ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ ሃገሬን ቆጨኝ ለራሴ
አለማወቄ
አለማወቄ
አለማወቄ
Written by: Verk