Lyrics

ወዲያ ማዶ እያየሁ የቅርቡን አርቄ ምነው እኖራለው የሄደ ናፍቄ የዓይኖቼ ዳርቻ እንባ እያቀረረ ብዙ ትውስታ አለ ከኔ አልርቅ ያለ የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር ያሳለፍነው እንዴት ይቅር ታስሬያለው በናፍቆትህ ሌትም ቀኑን በቅዠትህ ትውስታዬ የኔ ወዳጅ ያ ፍቅራችን ይታወስ እንጂ ይታወስ እንጂ ወደ ኋላ ሄዶ እየተመለሰ ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ ይሄው ደግሞ መሸ ዓይኔ ሊንከራተት መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር ያሳለፍነው እንዴት ይቅር ወይ ከንቱነት ምስኪንነት ያቺን ፍቅር ላልመልሳት ከምወደው ተለይቼ እኖራለው ደስታን አጥቼ ደስታን አጥቼ ወደ ኋላ ሄዶ እየተመለሰ ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ ይሄው ደግሞ መሸ ዓይኔ ሊንከራተት መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት ወይ ከንቱነት ምስኪንነት ያቺን ፍቅር ላልመልሳት ከምወደው ተለይቼ እኖራለው ደስታን አጥቼ ደስታን አጥቼ ደስታን አጥቼ ደስታን አጥቼ
Writer(s): Aster Aweke Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out