album cover
Merarche
album cover
Merarche wurde am 9. Februar 2024 von ela records als Teil des Albums Enzira veröffentlicht
AlbumEnzira
Released9. Februar 2024
Labelela records
BPM120
Melodizität
Akustizität
Valence
Tanzbarkeit
Energie

Songtexte

መራርጬ ቃላትን
ልገልፅላት ስሜቴን
በቃ ዛሬስ ነግራታለሁ ብዬ ወስንና
እፈራለሁ ብቅ ስትል አይኗን ሳየው ገና
አፍ የፈታሁበት ቋንቋዬ እሷ ፊት ከሚያንቀኝ
አይናፋርነቴ ላ'ፍታ ምን አለ ከኔ ብትርቀኝ
እሷ ከጉዳይም ሳትቆጥረኝ ትመላለሳለች
በፍቅሯ ልቤን ማጣቴን ምናለ ከአይኔ ባወቀች
ጉብዝናዬ ሲነገር ስሜ በሀገር ሲጠራ
ስርበተበት ተያዝኩኝ ለማናገር ስፈራ
ደፈር በል ንገራት የሚለኝ አበዛዙ
ጀግንነት መች ይሰራል ልብ ላይ ከተያዙ
መራርጬ ቃላትን
ልገልፅላት ስሜቴን
በቃ ዛሬስ ነግራታለሁ ብዬ ወስንና
እፈራለሁ ብቅ ስትል አይኗን ሳየው ገና
ሞኝነት የመሰለኝ እውነት በሰው ሳየው ያኔ
ዘንድሮ ቀልቤን አሳጣኝ በተራው ደርሶብኝ በኔ
ዛሬ ስል ያው ነገ ስል ሄደ ቀኑም እንደዘበት
ንገሩኝ ብልሃት ካለ እወድሻለሁ ለማለት
ጉብዝናዬ ሲነገር ስሜ በሀገር ሲጠራ
ስርበተበት ተያዝኩኝ ለማናገር ስፈራ
ደፈር በል ንገራት የሚለኝ አበዛዙ
ጀግንነት መች ይሰራል ልብ ላይ ከተያዙ
ጉብዝናዬ ሲነገር ስሜ በሀገር ሲጠራ
ስርበተበት ተያዝኩኝ ለማናገር ስፈራ
ደፈር በል ንገራት የሚለኝ አበዛዙ
ጀግንነት መች ይሰራል ልብ ላይ ከተያዙ
Written by: Ambachw Eshetu, Be Bright
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...