Songtexte

ልቤም ይሰወራል በናፍቆት ተሰርቆ መቼም አይመቸው ሰው ከሀገሩ ርቆ ስንቱን ባሕር አልፎ ዐይንሽ ካይኔ የዋለው ሰው ፈልጎ እንዳጣ ወገን እንደሌለው ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ክፉ አመል አስለምደሽኝ ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ምን ነክቶሽ ይሆን እያልኩኝ በሀሳብ አለቀ ጎኔ ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ በሀሳብ አለቀ ጎኔ ቻይው ናፍቆትሽን ብለሽ በርታ ፀና ብለሽ በርታ ፀና ብለሽ በርታ ፀና መልሶ እስኪያመጣኝ ያራቀኝ ጎዳና ያራቀኝ ጎዳና ያራቀኝ ጎዳና ከሀገር የሚወጣ ቢባል ተሰደደ ቢባል ተሰደደ ቢባል ተሰደደ ግድ ሆኖበት እንጂ ማን የሰው ወደደ ማን የሰው ወደደ ማን የሰው ወደደ በቃ ሲለዉ የኔን ማዘን እወጣለዉ ከመባዘን ከመናፈቅ ያኔ አርፋለሁ እስከዚያው ቀን በተስፋ አለሁ መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ ብጠብቂኝ ተበራትተሽ ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን ልቤም ይሰወራል በናፍቆት ተሰርቆ መቼም አይመቸው ሰው ከሀገሩ ርቆ ስንቱን ባሕር አልፎ ዐይንሽ ካይኔ የዋለው ሰው ፈልጎ እንዳጣ ወገን እንደሌለው ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ክፉ አመል አስለምደሽኝ ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ ምን ነክቶሽ ይሆን እያልኩኝ በሀሳብ አለቀ ጎኔ ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ በሀሳብ አለቀ ጎኔ አንቺስ ወገን አለሽ ሲያዝኑ የሚያፅናና ሲያዝኑ የሚያፅናና ሲያዝኑ የሚያፅናና እኔማ ከፋኝ ብል የት እሄደውና የት እሄደውና የት እሄደውና ከአንቺማ ብመጣ መንፈሴም ባረፈ መንፈሴም ባረፈ መንፈሴም ባረፈ በወጣልኝ ናፍቆት እየተቀረፈ እየተቀረፈ እየተቀረፈ ምን ቢከፋው የራቀ ሰው ወሳጅ እግሩን ሲመልሰው ይፅናናዋል ሲያገኝ ሁሉን እስከጊዜው ሰላም ያርገን መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ በጠበቅሺኝ ተበራትተሽ ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን ምን ቢከፋዉ የራቀ ሰው ወሳጅ እግሩን ሲመልሰው ይፅናናዋል ሲያገኝ ሁሉን እስከጊዜው ሰላም ያርገን መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ በጠበቅሺኝ ተበራትተሽ ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab, Amanuel Yilma Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out