album cover
Ho Temesgen
album cover
Ho Temesgen wurde am 20. November 1996 von Daniel Amdemichael als Teil des Albums Anbesa veröffentlicht
AlbumAnbesa
20. November 1996
LabelDaniel Amdemichael
SpracheEnglish
BPM171
Melodizität
Akustizität
Valence
Tanzbarkeit
Energie

Musikvideo

Musikvideo

Songtexte

ኦ ፡ ተመሥገን ኦ ፡ ተመሥገን
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
የምህረት ፡ ዓይኖችህ ፡ ይከታተሉኛል
የበደሌን ፡ ብዛት ፡ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ ሸፍኖታል
ሀዘንም ፡ ሲያጠቃኝ ፡ ከጐኔ ፡ ቆመሃል
መፅናናቴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አበርትተኸኛል
መፅናናቴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አበርትተኸኛል
ኦ ፡ ተመሥገን ኦ ፡ ተመሥገን
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ሁሉም ፡ በአንተ ፡ ሆነ
አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ የማወራው ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ የሆነ
እውነት ፡ ነፍሴን ፡ ላፍስስ ፡ ሥምህን ፡ ልወድሰው
የመዝሙሬ ፡ ዜማ ፡ ቅኔ ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
የመዝሙሬ ፡ ዜማ ፡ ቅኔ ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
ኦ ፡ ተመሥገን ኦ ፡ ተመሥገን
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
በሰው ፡ የተናቀ ፡ የተጣለውን ፡ ሰው
መደነቂያ ፡ እንዲሆን ፡ ጌታ ፡ ለክብርህ ፡ አቆምከው
ብርታት ፡ ትሆናለህ ፡ ሞገስ ፡ ትሆናለህ
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ኦ ፡ ተመሥገን ኦ ፡ ተመሥገን
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አስደናቂው ፡ ፍቅርህ ፡ ከሳበኝ ፡ ጀምሮ
ያደረክልኝ ፡ ውለታ ፡ አያልቅም ፡ ተቆጥሮ
ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥራ ፡ በምን ፡ ቋንቋ ፡ ልግለፅ
ማለት ፡ የምችለው ፡ ይኸን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ማለት ፡ የምችለው ፡ ይኸን ፡ ነው ፡ ውድዬ ፡ ተባረክ
ኦ ፡ ተመሥገን ኦ ፡ ተመሥገን
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ
Written by: Daniel Amdemichael Amdemariam
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...