Στίχοι

ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና ከጋረደን ጥቁር ደመና ጊዜው ይሆን እላለው እኔ የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና ከጋረደን ጥቁር ደመና ጊዜው ይሆን እላለው እኔ የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ እንዲያው አንዳንዴ ይገርማል ኧረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል እንዴት ተንዶ ፍቅራችን ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል በጊዜ አስታከን በዘመን ራስ መውደድን አስቀድመን ይቅርታ ራቀ ካፋችን ዝና እየተቀማ ልባችን አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን (እግዚኦ) ማረን ከክፋ አድነን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን ከክፋ አድነን አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ መሐረነ ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና ከጋረደን ጥቁር ደመና ጊዜው ይሆን እላለው እኔ የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና ከጋረደን ጥቁር ደመና ጊዜው ይሆን እላለው እኔ የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ በሀሜት በወሬ ታጅበን በግላዊ ምቾት ተከበን በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም ዘላለም ቋሚ ግን አንድ የለም ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን ክፋት ምቀኝነትን መርጠን ዘመን አለፈ ስንኖር የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን (እግዚኦ አንጽአነ) ከክፋ አድነን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን ከክፋ አድነን (እግዚኦ) አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና (እግዚኦ) አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ (ምግባሩ ሌላ) እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ መሐረነ አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን ከክፋ አድነን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን ከክፋ አድነን አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ ማረን ማረን ከክፉ አድነን
Writer(s): Simone Tsegay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out