album cover
Halelujah
album cover
Halelujah κυκλοφόρησε στις 4 Οκτωβρίου 2024 από Aster Abebe ως μέρος του άλμπουμ Hallelujah
ΆλμπουμHallelujah
4 Οκτωβρίου 2024
ΕτικέταAster Abebe
BPM130
Μελωδικότητα
Ακουστικότητα
Βαλάνς
Χορευτικότητα
Ενέργεια

Μουσικό βίντεο

Μουσικό βίντεο

Στίχοι

በሰላሙ ብዛት ቀለለ ችግሩ
አደገ ቁመቴ እያለ ነገሩ
ቀረ መዋከቤ በጠራኸኝ ሳርፍ
ተምራልኝ ነፍሴ አንተ ላይ ማራገፍ
ድምጿ ተቀየረ ተለወጠ ቃሏ
እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ
እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን
ለለወጥከው ኢየሱስ እንካ ዘላለሜን
ድምጿ ተቀየረ ተለወጠ ቃሏ
እዬዬን በእሰየው ያንተ በመሆኗ
እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን
ለቀየርከው ኢየሱስ እንካ ዘላለሜን
ተባረክ እልሃለሁኝ (8)
ተንበርክኬ አሸነፍኩኝ
እጅ ሰጥቼ ድል ነሳሁኝ
በጩኸቴ መዳን ሆነ
አበሳዬ ተከደነ
ተከትዬህ ከፊት ቀደምኩ
ያንተን ብዬ ከምን ጎደልኩ
ስፈልግህ ጸኑ እግሮቼ ሃይሌ ሆነኸኝ ተሟጋቼ
በመጨነቅ ስርአትህን
በመማጸን መጓደድን
በር በመዝጋት ክፉን ማምለጥ
እርዳኝ ብዬ ሁሉን መብለጥ
ከአንተ ሰምቶ የውስጥ ውበት
አቤት ብዬህ አለኝ ማለት
ከአንተ ዘግኖ ሞልቶ ማደር
ሆኖልኛል ስምህ ይክበር
ስኬቴ በአንተ መታመኔ
ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ
ውበቴ አንተን መጠጋቴ
ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ
ስኬቴ በአንተ መታመኔ
ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ
ውበቴ አንተን መጠጋቴ
ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ
አሃ
ሃሌሉያ (4) እላለው ሃሌሉያ
አሃ
ሃሌሉያ (4) እላለው ሃሌሉያ
በማለዳ ሃሌሉያ
በቀትር ሃሌሉያ
በምሽት ሃሌሉያ
በሌሊት ሃሌሉያ
ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሃሌሉያ
ሳይቀየር ሃሌሉያ
እላለው ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ያሌሉያ
ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ
ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ
አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ
ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ
Written by: Aster Abebe
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...