Credits
Lyrics
ግርማ ሞገሴ ነሽ
ለኔስ ግርማ ሞገሴ ነሽ
ለኔ ህይወት ለኔ መኖር
ለኔ ፍቅር
እስትንፋሴ ማን አለኝ ካንቺ በቀር
ማደሪያ ክብሬ እመቤቴ
ላመስግን አንቺን ከአንጀቴ
እምዬ (እምዬ)
ከፀጋ ፀበልሽ እርጪኝ
ፍቅርሽን መርቀሽ ስጪኝ
ኑሪልኝ (ኑሪልኝ)
ቀና በይልኝ ለኔ
አንቺው ነሽና ወገኔ
ወገኔ
ግርማ ሞገሴ ነሽ
ለኔስ ግርማ ሞገሴ ነሽ
መጠሪያዬም መኖሪያዬም
መድመቂያዬ
አንቺ እኮ ነሽ
እንድኖር በዚህች ዓለም
ዋልታዬም ምርኩዜ አንቺ ነሽ
አፅናኚኝ አይክፋህ ብለሽ ወዳጄ
(ወዳጄ)
አንቺው ነሽ ንብረቴ ለኔ
የዘመድ ወዳጅ ኩራቴ
እናቴ (እናቴ)
አትጪ አይክፋሽ ከቶ
አብቢ ጎተራሽ ሞልቶ አፍርቶ
ግርማ ሞገሴ ነሽ
ለኔስ ግርማ ሞገሴ ነሽ
ለኔ ህይወት ለኔ ፍቅር
ለኔ መኖር
እስትንፋሴ ማን አለኝ ካንቺ በቀር
ማደሪያ ክብሬ እመቤቴ
ላመስግን አንቺን ከአንጀቴ
እምዬ (እምዬ)
ከፀጋ ፀበልሽ እርጪኝ
ፍቅርሽን መርቀሽ ስጪኝ
ኑሪልኝ (ኑሪልኝ)
ማደሪያ ክብሬ እመቤቴ
ላመስግን አንቺን ከአንጀቴ
እምዬ (እምዬ)
ከፀጋ ፀበልሽ እርጪኝ
ፍቅርሽን መርቀሽ ስጪኝ
ኑሪልኝ (ኑሪልኝ)
አትጪ አይክፋሽ ከቶ
አብቢ ጎተራሽ ሞልቶ አፍርቶ
ዋልታዬም ምርኩዜ አንቺ ነሽ
አፅናኚኝ አይክፋህ ብለሽ ወዳጄ
(ወዳጄ)
Written by: Theodros Tadesse

