Letras

የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የሰው ዘር ሁሉ ያዳም ስህተት ይዞት ወደቀ ወደ ጥፋት ወደ ጥፋት ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ ሊከፍለው መጣ ለኃጢያት ዕዳ አወይ ለእኔ ዕዳ የኃጢያት ደሞዝ ነውና ሞት ሞቴን ሞተልኝ ሰጠኝ ሂወት ሰጠኝ ሂወት ኃጢያት ተሻረ ከእኔ ላይ በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ ቀራኒዮ ላይ በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ የጠፋሁትን ስለወደደ ኃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ በደሙ አንፅቶ ፃድቅ አስባለኝ ከደጉ አባቴ አሁን ታረቅኩ በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ በቀኙ ሆንኩ ደሙ አቀረበኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ፀሎት ነው የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ የማን ፀሎት ነው የሚያነፃኝ የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ የማን ምልጃ ነው የሚያጥበኝ ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ በአብ ቀኛ ያለ አንዱ ብቸኛ ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ ሰማይ ከእኔ ጋር ዕርቅ ያደረገው በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out