album cover
Maleda
3,625
Hip-Hop/Rap
Maleda fue lanzado el 15 de febrero de 2021 por Atgebam Alugn como parte del álbum Atgebam Alugn
album cover
Fecha de lanzamiento15 de febrero de 2021
Sello discográficoAtgebam Alugn
Melodía
Nivel de sonidos acústicos
Valence
Capacidad para bailar
Energía
BPM86

Letra

ማለዳ ማለዳ ቆንጆ ልጅ ባለዕዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ ማለዳ ቆንጆ ሸጋ ልጅ ባለዕዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ ማለዳ ማለዳ መተህ (ና ማለዳ)
አቦሉን ጠጥተህ ትመለሳለህ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ መጥቼ
ካቦልሽ ጠጥቼ
ተስመው ጉንጮቼ
ድምፅሽ ነፍሰ ገዳይ ልክ እንደ ማሪቱ
አላላውስ አለኝ ገብቼ ከቤቱ
የፍቅር ጨዋታ ቢሆን እንደ ጥንቱ
ድግስ ዛሬ ነበር የቤተ ዘመዱ
ውብ አለም ውብ አለም ሸጊቱ ሸጊቱ (ኢትዮጵያ)
ለእንዳንቺ አይነት ቆንጆ እኔ ልሁን መኩሪያ
እንደ ቤተ መንግስት እንደ ጃን አንበሳ
ስምሽ ታማ ብሎ ጎፍሮ ሚነሳ
(ስምሽ ታማብሎ ጎፍሮ ሚነሳ)
ተቸገረች አሉ ቡናዋ ቀጠነ (ና ማለዳ)
የቀረባት ሁሉ ዘመዷ እየሆነ (ና ማለዳ)
ቢቀጥን ቢወፍር ባይሆንላት እሱ (ና ማለዳ)
ማለዳ መጣለው ዋናው መቃመሱ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
የቤትሽ ደጃፍ ተሰርቶ ካፋፍ
ስንታየሁ ሞካሪ ላያገኙሽ ለፉ
ያመላልሰኛል ያንቺ ቡና ሱሱ
ሰክኖ እስክትቀጂው አቅምሺኝ ከቁርሱ
ከአቦሉም አደለም ከቶና በረካው
ካቀዳዱ ላይ ነው ጣሙ የሚለካው
ፍቅርሽ ያረገኝን እኔ ምን አውቃለው
እንዳበደረ ሰው አንድ አለኝ እላለው
እሳት እንኳን አልቆ ጠፍቶ ከምድጃው
ነደደ አከተመ ወይ ልቤ ሉባንጃው
መልኩ ያለየለት ፍቅርሽ ጉራማይሌ
ማለዳ ብቻ ነው አይገኝም ሁሌ
ተቸገረች አሉ ቡናዋ ቀጠነ (ና ማለዳ)
የቀረባት ሁሉ ዘመዷ እየሆነ (ና ማለዳ)
ቢቀጥን ቢወፍር ባይሆንላት እሱ (ና ማለዳ)
ማለዳ መጣለው ዋናው መቃመሱ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
ማለዳ (ና ማለዳ)
(ና ማለዳ)
Written by: Lij Michael
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...