Video musical

Incluido en

Créditos

PERFORMING ARTISTS
Neway Debebe
Neway Debebe
Performer
Washint
Washint
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Neway Debebe
Neway Debebe
Songwriter

Letra

ሲወዱሽ አታዉቂም እንዴ ሲያፈቅሩሽ ሲቀርቡሽ አትወጂም እንዴ ሲጠጉሽ ለመዉደድ መልስ ይሆናል ወይ ጥላቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ በጥርስሽ ታታልይና አስቀሽ በአይኖችሽ ታሻጊሪና አልመሽ ስትገይም አይታወቅሽ ስትረቺ አይ አንቺ ወይ አንቺ (ይገርማል) አይ አንቺ መማፀኔ ይሆን ወይ ያኮራሽ ለኔስ ሆኖብኝ ፍቅርሽ ጎርፍ ደራሽ እያሳሳቀ ድንገት ወሰደኝ ፍቅርሽ ኃይለኛ ማጥ ዉስጥ ዘፈቀኝ ፍቅርሽ ኃይለኛ ማጥ ዉስጥ ዘፈቀኝ ቀድሞ መረታት ሽንፈት ወየዉ ጉድ ራስሽን ወርቅም እኮ አልማዝ አረግሽ ዉድ ይቅር ብማፀንሽም ብትስቂ ሲያልፍ ይቆጭሻል አይዞሽ ጠብቂ ለኔም ቀን አለ አይዞሽ ጠብቂ ተይ ተይ ፍቅሬ ተመከሪ ተይ ተይ ተይ ችላ ማለትን ተይ ተይ ተይ ተይ ያስተዛዝባል ተይ ተይ ችግሬ ምንድነዉ እወቂ ተጠጊኝ ቅረቢኝ አትራቂ ሀሳቤን ጠይቂ ጠጋ ብለሽ በይኝ ምን ነበር በምክክር ሆኗል ቁም ነገር በአንቺ ከምቸገር (አዬዬዬይ) ሲወዱሽ አታዉቂም እንዴ ሲያፈቅሩሽ ሲቀርቡሽ አትወጂም እንዴ ሲጠጉሽ ለመዉደድ መልስ ይሆናል ወይ ጥላቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ በጥርስሽ ታታልይና አስቀሽ በአይኖችሽ ታሻጊሪና አልመሽ ስትገይም አይታወቅሽ ስትረቺ አይ አንቺ ወይ አንቺ (ይገርማል) አይ አንቺ ፍቅርን የሚያዉቀዉ ቅን ነዉ ያዉቀዋል እሽታ ከብዶ መች ይሳነዋል ተዉኩት ከእንጊዲህ ዳግም ላልኳትን ደና ሁኝ እኔም ከንቱ አልባዝን ደና ሁኝ እኔም ከንቱ አልባዝን ሰዎች መወደድ ለካስ ያኮራል ከጉራ ግምት ትዝብት ይጥላል አወይ ድካሜ ልፋት በከንቱ አላዉራዉ ይቅር ያንቺን ወይ ስንቱ አላዉራዉ ይቅር ያንቺን ወይ ስንቱ ተይ ተይ ፍቅሬ ተመከሪ ተይ ተይ ተይ ችላ ማለትን ተይ ተይ ተይ ተይ ያስተዛዝባል ተይ ተይ ችግሬ ምንድነዉ እወቂ ተጠጊኝ ቅረቢኝ አትራቂ ሀሳቤን ጠይቂ ጠጋ ብለሽ በይኝ ምን ነበር በምክክር ሆኗል ቁም ነገር በአንቺ ከምቸገር ሲወዱሽ አታዉቂም እንዴ ሲያፈቅሩሽ ሲቀርቡሽ አትወጂም እንዴ ሲጠጉሽ ለመዉደድ መልስ ይሆናል ወይ ጥላቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ በጥርስሽ ታታልይና አስቀሽ በአይኖችሽ ታሻጊሪና አልመሽ ስትገይም አይታወቅሽ ስትረቺ አይ አንቺ ወይ አንቺ (ይገርማል) አይ አንቺ መማፀኔ ይሆን ወይ ያኮራሽ ለኔስ ሆኖብኝ ፍቅርሽ ጎርፍ ደራሽ እያሳሳቀ ድንገት ወሰደኝ ፍቅርሽ ኃይለኛ ማጥ ዉስጥ ዘፈቀኝ ፍቅርሽ ኃይለኛ ማጥ ዉስጥ ዘፈቀኝ ቀድሞ መረታት ሽንፈት ወየሁ ጉድ ራስሽን ወርቅም እኮ አልማዝ አረግሽ ዉድ ይቅር ብማፀንሽም ብትስቂ ለኔም ቀን አለ አይዞሽ ጠብቂ ሲያልፍ ይቆጭሻል አይዞሽ ጠብቂ ተይ ተይ ፍቅሬ ተመከሪ ተይ ተይ ተይ ችላ ማለትን ተይ ተይ ተይ ተይ ያስተዛዝባል ተይ ተይ ችግሬ ምንድነዉ እወቂ ተጠጊኝ ቅረቢኝ አትራቂ ሀሳቤን ጠይቂ ጠጋ ብለሽ በይኝ ምን ነበር በምክክር ሆኗል ቁም ነገር በአንቺ ከምቸገር ችግሩ ምንድነዉ እወቂ ተጠጊ ቅረቢዉ አትራቂዉ ሀሳቡን ጠይቂ ጠጋ ብለሽ በይዉ ምን ነበር በምክክር ሆኗል ቁም ነገር በአንቺ ከሚቸገር ችግሬ ምንድነዉ እወቂ ተጠጊኝ ቅረቢኝ አትራቂ ሀሳቤን ጠይቂ ጠጋ ብለሽ በይኝ ምን ነበር በምክክር ሆኗል ቁም ነገር በአንቺ ከምቸገር
Writer(s): Samuel Alemu, Neway Debebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out