गाने

አብዱ ኪያር ይሉኝታ ሞቷል ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው የማላውቀውን ደስታ ደሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ እኔ ላንቺ ብለፋ ምናለ ምናለ አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ አንድ ጊዜ እንጂ ሁለቴ ሞት የለ መዳከሜን አይቶ ወዳጅ ዘመድ ራቀ ተስፋ ቤቴ ጠፋ ልቤም ተጨነቀ ግን ጥሎ ማይጥለው ይመስገን ፈጣሪ የውስጤን አየና ሰጠኝ ጥሩ አፍቃሪ ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ዬ... ዬ... የስ... ይሉኝታ ሞቷል ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው የማላውቀውን ደስታ ደሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ እኔ ላንቺ ብለፋ ምናለ ምናለ አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ አንድ ጊዜ እንጂ ሁለቴ ሞት የለ አይዞህ አይዞህ እያልሽ ይኸው ሁሉም አለፈ ለኔ ህይወት መሳካት ያንቺ ውበት ረገፈ ዛሬ ዘመድ ነኝ ባይ ያሻውን ቢያወራ ልቤ ላንቺ ብቻ ነው እንዳትሰጊ አደራ ምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ ሚደክመው ልብሽ ሚያወራው ሌላ የታል ይሉኝታ ካሁን በኋላ ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ዬ... ዬ... የስ... ይሉኝታ ሞቷል
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out