Video Musik
Video Musik
Dari
COMPOSITION & LYRICS
Michael Belayneh
Songwriter
Solomon Sahele
Songwriter
PRODUCTION & ENGINEERING
Michael Belayneh
Producer
Mickey Jano
Mixing Engineer
Melaku Sisay
Producer
Lirik
አንቺም እኔን ማለት ላትተዪ ደርሶ
የኔም አንቺን ማለት ላይቀር ተመልሶ
እንደው በከንቱ ሐሳብ ባልረባ ኩነኔ
ከ'ምነት አጎደልን ዘንድሮ አንቺና'ኔ
ልታይ ልታይ ብለሽ፣ ልታይ ልታይ ብዬ
አደባባይ አድረሽ፣ አደባባይ ውዬ
አንቺ ያለኔ ቀኑን፣ እኔ ያላንቺ ሌቱን
ለምደነው ነበረ፣ ወጥቶ መሰንበቱን
አንቺ እና እኔ ኖርን አንድ ሰሞን
አሞን አሞን
ክፉ ሐሳብ ቀድሞን
ዳንን ይቅር ተባብለን
ዕጣችን አንድ ናት ብለን ብለን ብለን
ይምራል አይቀጣም ፍቅር በክፉ ቀን
ቢጎመዝዝ ተውነው የሞከርነው ሰርቀን
ወድቀን ሳንሰበር ልቦናችን ነቃ
አይለመደንም አማትበናል በቃ
አንቺ እና እኔ ኖርን አንድ ሰሞን
አሞን አሞን
ክፉ ሐሳብ ቀድሞን
ዳንን ይቅር ተባብለን
ዕጣችን አንድ ናት ብለን ብለን ብለን
ቀና ቀና ሲያዩ በመካሰስ ፋንታ
ልብ ይለመልማል የታረመ ለታ
ይቅር ተባብለን ደስታ ቤቱ ገባ
ለ'ኔና ላንቺ ዓይነት ይህ ነው የሚገባ
አንቺ እና እኔ ኖርን አንድ ሰሞን
አሞን አሞን
ክፉ ሐሳብ ቀድሞን
ዳንን ይቅር ተባብለን
ዕጣችን አንድ ናት ብለን ብለን ብለን …
Written by: Michael Belayneh, Solomon Sahele


