album cover
Gilitun Simign
album cover
Gilitun Simign è stato pubblicato il 3 luglio 2019 da Minew Shewa Entertainment come parte dell'album Enfalot
AlbumEnfalot
3 luglio 2019
EtichettaMinew Shewa Entertainment
BPM84
Melodicità
Acousticità
Valence
Ballabilità
Energia

Video musicale

Video musicale

Testi

ግልጡን አልኩሽ እንጂ
ፈልጊኝ ሳልል ሩቅ ቦታ
ሳላውቅብሽ ሳልደብቅ
የልቤን ምንም እውነታ
ዘመዴ ነፍሴ ናፍቆት
የልቤ ጥም የዓይኔ አምሮቴ
ሩቅ ሄደሽ አትጪኝ ግልጡን
ያልኩሽን እርሱን አድምጪኝ
ምን ማለቱ ብለሽ አልፈሽ
አትፈልጊኝ ታጪኛለሽ
ምንም ማለቴ አይደል በቀር
ካልኩሽ ቋንቋ ካልኩሽ ፊደል
ዘመዴ ነፍሴ ናፍቆት
የልቤ ጥም የዓይኔ አምሮቴ
ሩቅ ሄደሽ አትጪኝ ግልጡን
ያልኩሽን እርሱን አድምጪኝ
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
እውነተኛ ወዳጅ እኔ ነኝ አፍቃሪሽ
ይህን አውቃለሁ ያልሺኝ ቅርብ እያልፈለግሺኝ
ምን ማለቱ ብለሽ አልፈሽ
አትፈልጊኝ ታጪኛለሽ
ምንም ማለቴ አይደል በቀር
ካልኩሽ ቋንቋ ካልኩሽ ፊደል
አንቺን አላርቅም ማንም
አንቺም ሌላ አታውቂም
ሁሌም በቋንቋሽ ሳወራ
ሁሌም እኔው ካንቺ ጋራ
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
ዘመዴ ነፍሴ ናፍቆት
የልቤ ጥም የዓይኔ አምሮቴ
ሩቅ ሄደሽ አትጪኝ ግልጡን
ያልኩሽን እርሱን አድምጪኝ
ምን ማለቱ ብለሽ አልፈሽ
አትፈልጊኝ ታጪኛለሽ
ምንም ማለቴ አይደል በቀር
ካልኩሽ ቋንቋ ካልኩሽ ፊደል
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
ያልኩ እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ ሩቅ አትሂጂ
ምንም የለም በቃ ምስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከርሱ በቀር
Written by: Zerubabbel Molla
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...