album cover
Lelit
49
Hip-Hop/Rap
Lelit è stato pubblicato il 27 maggio 2022 da Birrz Studio come parte dell'album Lewt
album cover
AlbumLewt
Data di uscita27 maggio 2022
EtichettaBirrz Studio
Melodicità
Acousticità
Valence
Ballabilità
Energia
BPM97

Video musicale

Video musicale

Crediti

COMPOSITION & LYRICS
Kidus H Worku
Kidus H Worku
Songwriter
SAMUEL TEFERI
SAMUEL TEFERI
Songwriter

Testi

ለመጀመር አዲስ ስራ ሆኜ ስቱዲዮ
አዲስ ቀንን የሚከተል የሚገኘው በልጦ
አወርዳለው አወጣለው ከየት እንደምጀምር
ግራ ገብቶኝ ማወቅ ውስጥ ያለውን ነገር
በሃሳብ ተወጥሮ አይምሮ
ከመሸ በህዋላ ሰርዤ ቀጠሮ
ተነስቼ ወጣው ላስብ ምን እንደጎደለ
ካገኘው ልፈልግ በከተማው ጥበብ የተሳለ
የሚተኩስ የሚያነሳ ህይወት የኔ ምላጭ
እውነት የሚያፅፈኝ የሚያረገኝ ቀራጭ
በዚ ሰዓት ትዝ ይለኛል ከጓደኞቼ ጋር
ያበድንበት ያ ጊዜ ለኔ አይዘነጋ
ይሄ ለሊት አለው ሚስጥር እንዳትጥራጠር
አለው የተለየ ነገር ልዩ የህወት ቀመር
ለአንዳዱ እረፍት ለአንዳንዱ ሀፍረት
ለአንዱ ስራ ልቤ ለሊት ሲያይ የ አንድ ቀን ስህተት
ለተመቸው ለመምረጫ ለተራበው አደን መውጫ
የቂም በቀል ፍትህ መስጫ የፍርድ ቀን መቀጣጫ
ለአደለው ደስታ ብቻ ስትሆን ይቺ ምሽት
መርሻ ነች ለተከፋው ላለው በብስጭት
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ…)
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ…)
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
በዚህ ምሽት እየተጓዝኩ በአካልም ሃሳብ
በጨረቃ እየፈለኩ ጥበብ የሚሆነኝ እርካብ
የመንገዱ መብራት ግማሹ በርቶ ግማሹ የጠፋው
መስሏል የኛን ህይወት ለአንዱ ጎድሎ ለአንዱ እንደሚሞላው
ሳይ የወደቁት በየጥጉ በእድሜ የገፉት ምስኪን ህፃናት ወጣቱ
በመከራ የሚኖሩት በብርድ በ ሃሩሩ
ይቀየራል ያስተዋለ ለነሱ የህይወት መነፅሩ
ጠርቶ ስማዩ ኮኮቦች ተበትነዉ
ልዩ ስሜት አለው ጨረቃዋ ስታየኝ እያየው
በነፋሻው አየር እየሄድኩኝ በዝግታ
አስተዋልኩኝ ሌላ የዉብ ገፅታ
መኪናዋ ተውጣለች በጫጫታ
እየሳቁ ነው ጥንዶቹ ተመስጠው በጫዋታ
ያስታውቃል እንደሆነ እየተደሰቱ
ከጠርሙሱ ተቀባብለው እየተጎነጩ
ደስታቸው እንዳይጨልም ባይነዱ ተመኘው
በእንባ እንዳይሸኝ የደስታ ቀናቸው
አይታወቅ አጋጣሚው ስንቱ ቀርቷል ወቶ
ፍም በሚሳምባት በዚች ለሊት ለደስታ ጠጥቶ
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ…)
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ…)
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
ከተማዋ ቃል አላት እኔ እየሰማሁት
እየተጓዝኩ የሷን ሚስጥር በአይኔ አየሁት
ይገርመኛል ይሄ ቦታ አሁን ያለሁበት
ነው የሚመስለው ግርግሩ ጊዜ የሌለበት
በግራ እና በቀኝ የምሽት ቤቶቹ ተደርድረው
በመብራትም ሰፈሩን አድምቀው
ተሰልፈው አውራ እንስቶች በየበሩ
ጦርነት ይመስላል በአጭሩ ደንበኛ ሲስቡ
ይሄ ሁሉ አስገርሞኝ ልቤን የደነቀው
መገኘታቸው ነው አዎ ትምህርት ቤት ከበው
ተፅኖውን እያሰበኩት ነገን ለሚያስቡት
በአንድ ቀን ስህተት በዚች ምሽት ሁሉንም ለሚያጡት
በዚህ ስህተት በአጋጣሚ ወድቃ ከሃዘን ስካር
የምትኖረው ነፍስ እየቆረጠች እየሸጠች ትዳር
አዳር እጣፋንታ ገፍታ ከቤትዋ ያስወጣቻት
ከዚ አዙሪት እንድትወጣ አምላክ ሌላ እድል ቢሰጣት
ሲሸጥ የውሸት ፍቅር ሲሸጥ የውሸት ሳቅ
አይቻለው ስትበላ እውነት በዚች አለም ጭራቅ
ብዙ አሳየቺኝ እንዳልረሳት አልፋ
ጉድ አበቃችኝ የኔንም ለሊት ታሪኳን አፅፋ
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ… )
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
ፍቅር የለም በከተማዋ ልብ (አዎ…)
ፈረሰ ብርሃን የጊዜ ግንብ (አዎ …)
Written by: Kidus H Worku, SAMUEL TEFERI
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...