ミュージックビデオ
ミュージックビデオ
クレジット
PERFORMING ARTISTS
Haile Roots
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Hailemichael Getnet Ayele
Songwriter
歌詞
መርጦ ባልመጣበት ዘሩን አስቦ
በሚለያይ ትውፊት ቢነጉድም ተስቦ
መሆኑን ያልረሳ የአንድ አብራክ ፍሬ
ሰው አላት ሰው ሆኖ የቆመላት ዛሬ
ኡ ሰው አላት
አገሬም ሰው አላት
ለነፃነት
ክብሯ የቆመላት
ኡ ሰው አላት
አገሬም ሰው አላት
የሁላችን
መጠሪያ የምንላት
ምን ቢያማትም ውስጧን ክፋት ቀን ገዝቶ
በዝቶ አዛኝ ቅቤ አንጓች አውቅልሽ ባይ ዋሽቶ
አላት ሰው ከጭንቋ የሚያድን ደርሶ
በእውነት ህመሟን የሚያክም መልሶ
ኡ ሰው አላት
አገሬም ሰው አላት
ለነፃነት
ክብሯ የቆመላት
ኡ ሰው አላት
አገሬም ሰው አላት
የሁላችን
መጠሪያ የምንላት
ቢፈስ አቅንቶ
ቢጎላት ሞልቶ
በልዩነት ተስማምቶ
የማያቆስላት
በእኔ እበልጥ እኔ
በሚለይ ሰው ቅኔ
ቢፈስ አቅንቶ
ቢጎላት ሞልቶ
በልዩነት ተስማምቶ
የማያቆስላት
በእኔ እበልጥ እኔ
በሚለይ ሰው ቅኔ
በአጉል ወግ በተረት በኢዝም እስኪዝም
በዘር በጥላቻ ማንነቲዝም
ሊንድ መሠረቷን ቢገዘግዝም
አይፈርስም ቢገፋ ቢወዛወዝም
በአጉል ወግ በተረት በኢዝም እስኪዝም
በሚለይ ሰው ከሰው ማንነቲዝም
ሊንድ መሠረቷን ቢገዘግዝም
ትኖራለች ፀንታ አትደበዝዝም
በአጉል ወግ በተረት በኢዝም እስኪዝም
በዘር በጥላቻ ማንነቲዝም
ሊንድ መሠረቷን ቢገዘግዝም
አይፈርስም ቢገፋ ቢወዛወዝም
በአጉል ወግ በተረት በኢዝም እስኪዝም
በሚለይ ሰው ከሰው ማንነቲዝም
ሊንድ መሠረቷን ቢገዘግዝም
ትኖራለች ፀንታ አትደበዝዝም
Written by: Hailemichael Getnet Ayele