クレジット

PERFORMING ARTISTS
Lastarock
Lastarock
Vocals
COMPOSITION & LYRICS
Michael Dires Tadesse
Michael Dires Tadesse
Songwriter
Zekeriya Fekadu Sesero
Zekeriya Fekadu Sesero
Songwriter
PRODUCTION & ENGINEERING
Nerliv
Nerliv
Co-Producer

歌詞

ልቅም ጥንቅቅ ያለች የሰው መና
ሽሞንሟና
የሂዎት እጣ ሎተሪው ደርሶኝ አንችን
እድል ሲቀና
አማረ ቤቴ መንገዴ በ ፍቅር ፀና
ማር አካል ገላ
አቧራው ጨሰ ሞቀ ድግሱ ደራ
ስንል ሀይሎጋ
ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋዎ
ያስፈለኳት በእግር በፈረስ
ቢያሻኝ መዳኒት አጋር ለነብስ
ተገኝታለች ቀናኝ በለስ
በልቤ አዳራሽ ስትል ሽር ፈሰስ
እንደ ሃገርሽ ነይ እንደ ሃገሬ
ልሁን መከታሽ ሁኝ እመቤቴ
ብንሆን አንድ ሙሉ ነው ስሟ ስሜ
ቃል አክብራ ከብራ በቃሌ
መውደድ ገሩ አድርጎኝ ጉሽም
ሸጋ ይዥ እሽክም እሽክም
ይመስገን ነው ሁሉም አሻም
ሂዎት ጣፍጧል ሁነሽ ቅመም
አየው አለው አለው እና
በማተቡ ይሄዉ ፀና
የኛው ጎጆ በኛው ቀና
ማገር ሁኘሽ አንችም ባላ
እሰይ ነይ ነይ የኔ አበባ
ይዥሽ ቶሎ ቤቴ ልግባ
አረ እሰይ ነይ የኔ ደስ ደስ
ይዥሽ ቶሎ ቤቴ ልድረስ
ልቅም ጥንቅቅ ያለች የሰው መና
ሽሞንሟና
የሂዎት እጣ ሎተሪው ደርሶኝ አንችን
እድል ሲቀና
አማረ ቤቴ መንገዴ በ ፍቅር ፀና
ማር አካል ገላ
አቧራው ጨሰ ሞቀ ድግሱ ደራ
ስንል ሀይሎጋ
ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋዎ
ወጉን አትስሚ ቢሉሽ ስለኔ
የለውም ፍሬ ብትበየው ነው ጥሬ
ሰው ምቀኛ ነው ይሉሻል ቅሪ
አለው ወዳጅሽ ምከሪ ከኔ
ያይንሽን ቋንቋ ሚረዳው ልቤ
ደሞ ምን ጠቅሞን ወሬ ነጋሪ
አድርጊ ብር አምባር ለአንገትሽ ድሪ
ለጆሮም ዳባ ነገር እንዳትሰሚ
ማንነትሽን ጓዳ ገመናሽን
ከኔ በላይ ማን ሰው ያውቅና
ከፈለኩሽ አንችም ከወደድሽ
ማን አግብቶት ወስኖ ለእኛ
ሽቶ ለእናትሽ ወርቁን ለአባትሽ
ከተቀበሉ ከፈቀዱማ
ከመረቁ እሽ እንድዎስድሽ
ነይ በይ ተነሽ እንጨፍርማ
ይሰማል ወይ ደጅሽ
ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሀይሎጋዎ
Written by: Michael Dires Tadesse, Zekeriya Fekadu Sesero
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...