クレジット
PERFORMING ARTISTS
Bezuayehu Demissie
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Yonas Mulatu
Songwriter
歌詞
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
ክተት አዋጅ አለ ነጋሪት ሳይመታ
ፍቅርሽ ድል አረገ የማታ የማታ
ዘምተሽ ስትማርኪ ማንም አላገደሽ
ከሰውነቴ ጋር አንዴ ተዋህደሽ
ከሰውነቴ ጋር አንዴ ተዋህደሽ
ከመደቡ አቅፈሽኝ ከጎኔ ተኝተሽ
እንደ ማገዶ ፍም ይሞቃል ትንፋሽሽ
የውዴን መኖሪያ ሳውቀው ቦታውን
ታሳየኝ ጀመረ ጀርባ ጀርባውን
ታሳየኝ ጀመረ ጀርባ ጀርባውን
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
ተሳቀብኝ አሉ ተሳለቁብኝ
አንቺን ሳላገኝሽ ስባዝን ሲያዩኝ
ዳኛውም አይፍረድ ጠበቃም አልሻ
ያኔ አየው የለም ወይ የልቤን መድረሻ
ያኔ አየው የለም ወይ የልቤን መድረሻ
ቢነጋም አይሄድም ቢመሽም አይርቅም
ያንቺ ፍቅር ጅል ነው ወዳጁን አይወድም
ያሞኛል ያቄላል ብልህ ያጃጅላል
ጎበዙ ፍቅርሽ ነው ሰው በቁም ይሰርቃል
ጎበዙ ፍቅርሽ ነው ሰው በቁም ይሰርቃል
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
ምስክር እያየ በግልፅ ባ'ደባባይ
በግልጽ ባ'ደባባይ
በተፈጥሮ ውበት ሳትታጠቅ ገዳይ
ሳትታጠቅ ገዳይ
እዚያም ዘው እዚያም ዘው ከሆነ ያንቺ ዕጣ
እኔም እገባለሁ አዲስ ቤት አላጣም
ቆርጠሽ ከተነሳሽ በይ እንሰናበት
ለኔ አዲስ አይደለም እንግዳ መሸኘት
ለኔ አዲስ አይደለም እንግዳ መሸኘት
ቢነጋም አይሄድም ቢመሽም አይርቅም
ያንቺ ፍቅር ጅል ነው ወዳጁን አይወድም
አንቺስ ይህን ያህል ለምን ትለፍያለሽ
ሰርፀሽ በሰው ልብ ውስጥ እሳት ትጭርያለሽ
ሰርፀሽ በሰው ልብ ውስጥ እሳት ትጭርያለሽ
Written by: Yonas Mulatu

