ミュージックビデオ

歌詞

ድሬ ሀረር ድሬ ሀረር እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ ድሬ ላይ ያለችዉ ዋኔ ዋኔ እያለች በእምባ ስትለየኝ ከልቤ አልጠፋ አለች ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ መገን የድሬ ልጅ ፀባይ ምግባራቸዉ እንግዳ ያለምዳል አቀራረባቸዉ ከማሽላዉ ዛላ ቀንጥሳ ጋብዛኝ ተላወሰ ሆዴ መዉደድ ዘርታብኝ አቦ ሰላም ያግባህ ብላ እንደሸኘችኝ እንዳይጨንቀኝ ምነዉ በተከተለችኝ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ ድሬ ላይ ያለችዉ ዋኔ ዋኔ እያለች በእንባ ስትለየኝ ከልቤ አልጠፋ አለች ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ ኮልተፍ ኮልተፍ ሲል ጣፋጭ አንደበቷ ቃሏም ይናፍቃል እንኳን ደም ግባቷ እፎይ ብዬ አልተኛ ሰላምታ ልኬብሽ እንዳሻኝ አርጉልኝ አልል እንደሰዉ ሆኜ ምን ለብሼ ልምጣ እስኪ አንቺዉ ላኪብኝ ወጉን አላዉቅበት ሽርጥ አያምርብኝ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ ድሬ ላይ ያለችዉ ዋኔ ዋኔ እያለች በእንባ ስትለየኝ ከልቤ አልጠፋ አለች ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ ከዞርኩበት ሁሉ ድሬን ምን አደላት እንደፍራፍሬዉ የሰዉ ዉብ ሸጋ አላት ከድሬ ልጅ ፍቅር ትዝታ የያዘዉ አዋሽ ቁርስ አይበላ ሂርና ምሳ የለዉ እዩት ብርቱ ልቤን መዉደድ ያከነፈዉ ከባቡሩ ቀድሞ አዳሩ ድሬ ነዉ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ
Writer(s): Elias Woldemariam, Negash Fiseha Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out