album cover
Guadegna
album cover
Guadegna은(는) {albumName} 앨범에 수록된 곡으로 2019년 7월 3일일에 Minew Shewa Entertainment에서 발매되었습니다.Enfalot
앨범Enfalot
2019년 7월 3일
라벨Minew Shewa Entertainment
BPM88
멜로디에 강한 음악
어쿠스틱 악기 중심
발랑스
춤추기 좋은 음악
에너지

가사

የራሴን ትቼ ሳይ የሌላን ሰው
እንከን ጉድፉን ጠርጎ እንዲያነሳው
የታየኝ መስሎኝ ጓዴን ሳምሰው
ማየቱን ሳላይ ጭራሽ ታውሬ
ከንቱ እሩጫ ጥድፊያ ለወሬ
ምን አይነት አመል ከንቱ ባህሪ
ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ...
ውስጤ ቆሽሾ ውጪውን ሳጸዳ
ባላይ በላዩ ከዚያው ስቀዳ
ሳይታወቀኝ ስከምር ዕዳ
እግሬ እያቦካ ሲያጨቀይ ሰፈር
ከእጄ የፈሰሰው ውሃው ሲጨመር
ያቀናሁ መስሎኝ ሳውክ ሰው መንደር
ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ...
አጥርቶ ዓይቶ ዓይኔን ላጸዳ
ከሸፈነኝ እንደ ግድግዳ
ጥልቅ ነው አክብሮቴ በሕይወተለ
የመከረኝ ያ መልካም ወዳጅ
ላተረፈኝ ከጥፋቱ ደጅ
እሱ ነው ጓደኛ አንደኛ
ሂደው ተራመደው ተጓዘው ከፊትህ
አዲስ ምሰሶ ወጣ ላዲስ መሠረተህ
አይዞህ አትነጋገር ከተውከው ማንነት
ልቀቀው ይሂደው ማንም ከሌለበት
ቆሞ እየሸፈነህ ሆኖ እንደ ግድግዳ
ደራሽ ወዳጅ ይዘህ እንዴትስ ትጎዳ
ተመልከት ወዳጄ የቆምንበት ቦታ
የታመሰው መንደር ተካሰ በደስታ
ኦ ኦ ኦ
Written by: Zerubabbel Molla
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...