크레딧

실연 아티스트
Tsehay Yohannes
Tsehay Yohannes
실연자
작곡 및 작사
Tsehay Yohannes
Tsehay Yohannes
작사가 겸 작곡가

가사

አበባ ሸንኮራ ትርንጎ ዘለላ
ነሽና እንጆሪ የኔ ማር ወለላ
ህመሙም ስቃዪም በኔው ይለፍልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
እንደ አበባ ፈክተን እንደ ፀሀይ ደምቀን
ልባችን ሳይሻክር በፍቅር ተውበን
አንቺ እኔን ስትይ እኔ አንቺን አንቺን
ሌላው ትምርት ይቅሰም ከሁለታችን
ሌላው ትምርት ይቅሰም ከሁለታችን
አበባ ሸንኮራ ትርንጎ ዘለላ
ነሽና እንጆሪ የኔ ማር ወለላ
ህመሙም ስቃዪም በኔ ይለፍልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
ንፋስ እንደገፋው አንፍገምም
ሰው አለ በማለት አንፍረከረክም
የቀና ያወራል ብዙ ይናገራል
ቢሆንም ልብሽን ልቤ እኮ ያውቀዋል
ቢሆንም ልብሽን ልቤ እኮ ያውቀዋል
ወረት ያልተጫነው ጊዜ የማይለውጠው
ቁጣና ብስጭት ንዴት የማይገዛው
ለአዲስ ፍቅረኞች ምሳሌ ሚሆነው
ተድላና ደስታችን ቋሚው ፍቅራችን ነው
ተድላና ደስታችን ቋሚው ፍቅራችን ነው
አበባ ሸንኮራ ትርንጎ ዘለላ
ነሽና እንጆሪ የኔ ማር ወለላ
ህመሙም ስቃዪም በኔ ይለፍልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
እኔው ልሸከመው አንቺን ደስ ይበልሽ
ድብቁን አይቼ ሚስጥሩን አውቄ
ዳግም በአዲስ መንፈስ እንዳዲስ ታጥቄ
ሰው እንድሆን ሁሌ የምሰጪን ምክር
ሳስበው አርቄ ያረካኛል ዘውትር
ሳስበው አርቄ ያረካኛል ዘውትር
Written by: Tsehay Yohannes
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...