album cover
Lewt
1,041
Hip-Hop/Rap
Lewt은(는) 앨범에 수록된 곡으로 2022년 5월 27일일에 Birrz Studio에서 발매되었습니다.Lewt
album cover
앨범Lewt
발매일2022년 5월 27일
라벨Birrz Studio
멜로디에 강한 음악
어쿠스틱 악기 중심
발랑스
춤추기 좋은 음악
에너지
BPM97

뮤직 비디오

뮤직 비디오

크레딧

작곡 및 작사
Kidus H Worku
Kidus H Worku
작사가 겸 작곡가
SAMUEL TEFERI
SAMUEL TEFERI
작사가 겸 작곡가

가사

ተጀምሮ እስከሚያልቅ ሁሉም በሂደት ውስጥ ነው
ሊንበረከክ በጊዜ ፊት ሲታገል የኖረው
ተሸንፎ እንደሚቀየር ለዘላለም ያለው
አይመስለንም እንጂ ለውጥ ተፈጥሮ ነው
የታሪክ አውነቱም መሃል ይረሳል በዘመን
በሀል ይቀየራል በቦታ እና በቀን
ሰው ለውጥ እምቢ ቢል አዎ ትነሳዋለች ድል
እያንቆራጠጠች ይቺ የጊዜ ብትር
ሆኖም በፍላጎት መቀያየር ይቻላል
ብልህ በራሱ ሣይደርስ ከሚያየው ይማራል
ምክንያቱም አሁን ላይ ህይወት ጨዋታ አይደለም
እድሜን እየገፉ አይባልም አይኖር ዘላለም
ከትላንቱ መቼም ዛሬ ተገኝቷል ተሸሎ
ቢጨምርም ሃላፊነት ባይጫንም ቀሎ
ግን ባለፈው ጠንክሪያለው ችዬ እንደምወጣው
ተምሬበት በጥፋቴ ቁጭት ልቤን እየቀጣው
ጨርሻለው ብዬ ሁሉን ቀይሪያለው
አልገባኝም እንጂ ለካ ለውጥ ተፈጥሮ ነው
ደስታ ያለበትን እውነት ስንቀበል
ያኔ ያቆማል ስቃይ ከራስ ጋር መታገል
ከሀሳብ ጋር ትግል
ስጮህ ጥያቄ ሥል
መልስ ሆነኝ ሰማይ
ጨልሞ ነጋ ሳይ
ከሀሳብ ጋር ትግል
ስጮህ ጥያቄ ሥል
መልስ ሆነኝ ሰማይ
ጨልሞ ነጋ ሳይ
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አስተውል ሰው ይቀየራል ባሳለፈው
ሲረገም አይተናል ብለን የባረከው
የምር ማን ማንን ይዳኛል በዚች ምድር
የትኛው ቤት ንፁ ያልሰረቀ የሌለበት ሚስጥር
የሌለበት ክህደት አዎ የሌለበት ቅናት
የሌለበት ውሸት አዎ የሌለበት ጥፋት
ግን ይኖራል ተቻችሎ በዛች አንድ ምክንያት
ማንነቱ ነች የቤቱ አይችልም ሊተዋት
ሰው ነው ልክ እንደቤቱ ነው
ፍቅርን ያስተማሯት ፍቅርን እንደምትወርሰው
በጥላቻም ያሳደጉት ከፉ እንደሚቀርፀው
ለዛ ነው ሀገራችን አዎ እኛን የምትመስለው
ያ ጉጉት በልጅነት ሁሉን ለማሳካት
ፍቅር ገንዘብ የሚያምር ቤት ደስታ የማያልቅባት
ማለም ማለም ብቻ እድሜ እስኪያነቃ
ካልከፈሉ ዋጋ ይቺን አለም መግዛት አይቻልም ለካ
በቃ ሳይረፍድብኝ እኔም ሀሳቤን አምኜው
ልቤን ዝም በልልኝ አዎ እያልኩኝ ቀይሬው
በዛም በዚም Hustle አዎ ድርሻዬን ላገኘው
ሳይፈታ እንዳይቀር ተው እኔም የማልመው
ከሀሳብ ጋር ትግል
ስጮህ ጥያቄ ሥል
መልስ ሆነኝ ሰማይ
ጨልሞ ነጋ ሳይ
ከሀሳብ ጋር ትግል
ስጮህ ጥያቄ ሥል
መልስ ሆነኝ ሰማይ
ጨልሞ ነጋ ሳይ
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
አዎ ለውጥ ግድ ነው
Written by: Kidus H Worku, SAMUEL TEFERI
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...