크레딧
실연 아티스트
Afrika - Artists of Ethiopia
실연자
Tamrat Desta
실연자
작곡 및 작사
Habtamu Bogale
작사가 겸 작곡가
가사
አይከብድም ወይ በልብ ያለን ሰዉ መርሳት
አይከብድም ወይ አይከብድም ወይ
እስኪ አንቺኑ ልጠይቅሽ ባንዴ ልብ
ይቆርጣል ወይ
አይከብድም ወይ በልብ ያለን ሰዉ መርሳት
አይከብድም ወይ አይከብድም ወይ
እስኪ አንቺኑ ልጠይቅሽ ባንዴ ልብ
ይቆርጣል ወይ
እንዴት እንዳቃተኝ እኔን ምነው ባየሽ
ተጓዡ ልቤ ደጋግሜ ብገስፀው ባሰበት
ሆድ ሊያብሰኝ ባሰበት
እንኳን ሊመለስ አንቺን እያለ መባዘኑን ገፋበት
ማረፊያ ሳጣ ያንን ጊዜ ዞር ብዬ ሳስበው
ልንለያይ የቻልነው
ከመለያየት ሌላ አማራጭ አልነበረም ወይ እላለሁ
አማራጭ ነበር ሳስበው እኔ
እምቢ አልሽ እንጂ እምቢ ስል እኔ
እንዲ ላትረሽኝ ው ላይረሳሽ ጎኔ
(እርሳት ይሉኛል)
እርግፍ አድርጌ አንቺን ለመርሳት እኔ አልቻልኩኝም
(እርሳት ይሉኛል)
ወሬ አይደበቅ አንቺም ጨክነሽ አልረሳሽኝም ፍቅሬ አልተዉሽኝም
(እርሳት ይሉኛል)
ታድያ ካቃተዉ ልባችን መቁረጥ ብንወስንም
(እርሳት ይሉኛል)
ባለማስተዋል የሆነ ስህተት ሳንሰራ አንቀርም ያኔ አላየንም
አይከብድም ወይ በልብ ያለን ሰዉ መርሳት
አይከብድም ወይ አይከብድም ወይ
እስኪ አንቺኑ ልጠይቅሽ ባንዴ ልብ
ይቆርጣል ወይ
እንዴት እንዳቃተኝ እኔን ምነው ባየሽ
ነጎደ ጊዜዉ እያየነዉ ገሰገሰ እንደቀልድ
እድሜም ሄደ እንደቀልድ
ስንት ትዝታ ማየት ስንችል ስንት ፍቅር መዋደድ
አልሆነኝ እኔ
አንቺም ይኸዉ ካልተለየሽ ከጭንቀት
ወይ ካልሸሽ ከጭንቀት
ይቅር ለእግዚአብሔር ብንባባል እስቲ ምን ነበረበት
ተይ አልረፈደም አሁንም የኔ
በእግዜሩ መንገድ እንሂድ በወኔ
በይ አንቺም ተይዉ በይ ተዉኩት እኔ (በይ ተውኩት እኔ)
(እርሳት ይሉኛል)
እኔ አምኛለሁ ያኔ ማጥፋቴ አሁን ገብቶኛል
(እርሳት ይሉኛል)
ከበቂ በላይ አንቺን ማጣቴ አስተምሮኛል ብዙ አሳይቶኛል
(እርሳት ይሉኛል)
መቼም ከስህተት የፀዳ የለም ስህተት ሰርተናል
(እርሳት ይሉኛል)
ታድያ ካለፈዉ ፍቅሬ ብንማር ቆይ ምን ይለናል ፍቅር ይሻለናል
Written by: Habtamu Bogale

