album cover
Endemnesh
album cover
Endemnesh은(는) {albumName} 앨범에 수록된 곡으로 2024년 6월 28일일에 Abdu Kiar에서 발매되었습니다.Papapa
앨범Papapa
2024년 6월 28일
라벨Abdu Kiar
BPM114
멜로디에 강한 음악
어쿠스틱 악기 중심
발랑스
춤추기 좋은 음악
에너지

가사

አላምደሽ አላምደሽ ስትርቂኝ ተጎዳሁ
ተዘባርቆብኛል አደባባይ ጓዳው
ሰው አለ ሰው የለም ይመጣል ፈገግታሽ
እልም ይላል ልቤ ርቆ በትዝታሽ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
ይሄ ያላንቺ ኑሮ
ሊያሳብደኝ ነው ዘንድሮ
አቅም አሳጥቶኛል
ከሰው ጋር መኖር ከብዶኛል
ምነው ምነው እያሉ ጥያቄ ያበዙብኛል
ባለፍኩበት ጎዳና ይጠቋቆሙብኛል
እኔ በናፍቆት ብዛት ራሴን ጥዬልሻለሁ
እሷስ ብቻዋን እዛ እንዴት ትሆን እላለሁ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
እናፍጥነው እንተያይ እንጂ
ህይወትማ ይከብዳል ያላንቺ
ካንቺ ጋራ ስሆን ለጉድ የሚሮጠው
ብቻዬን ሲያገኘኝ ጊዜን ምን ጎተተው
አንድ ቀን እንዳመት እየረዘመብኝ
አይንሽን ማይበት መምጫሽ ቀን ራቀብኝ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
ልጠይቅሽ ልጠይቅሽ ውዴ
ናፍቆት እንዲ ጤና ይነሳል እንዴ
ይሄ ያላንቺ ኑሮ
ሊያሳብደኝ ነው ዘንድሮ
አቅም አሳጥቶኛል
ከሰው ጋር መኖር ከብዶኛል
ወፈፍ አድርጎ ያስቀበጣጥረኛል
ብቻዬን አወራለሁ ምትሰሚኝ ይመስለኛል
የኔ ጤና ተዛብቶ መስመር እያስለቀቀኝ
ያንቺ ነገር ብቻ ነው ጧት ማታ የሚያስጨንቀኝ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
እናፍጥነው እንተያይ እንጂ
ህይወትማ ይከብዳል ያላንቺ
እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ
ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ
ልጠይቅሽ ልጠይቅሽ ውዴ
ናፍቆት እንዲ ጤና ይነሳል እንዴ
እንደምነሽ
እንደምነሽ
Written by: Abdu Kiar Kahssay
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...