album cover
Simagne
album cover
Simagne은(는) {albumName} 앨범에 수록된 곡으로 2024년 12월 31일일에 ela records에서 발매되었습니다.Qen Beqen
앨범Qen Beqen
발매일2024년 12월 31일
라벨ela records
BPM87
멜로디에 강한 음악
어쿠스틱 악기 중심
발랑스
춤추기 좋은 음악
에너지

가사

የመስኩ ትንፋሽ ያ ዜመኛ
ቅኔ ዘራፊው ደግ እረኛ
ወዲያ ሲል ልቤ ማዶ ማዶ
እየታዘበኝ ከብት አግዶ
ኧረግ አንተው ብርቱ ዓይናማ
አለኝ ድንገት ስማኝ እማ ስማኝ ስማኝ ስማኝ ስማኝ
ስማኝ… አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ… ማንነትህን ዞረህ ቃኝ
ስማኝ… አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ… ማንነትህን ዞረህ ቃኝ ስማኝ ስማኝ ስማኝ
አዝሎ ሰማይ ተስፋ አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ብሩህ ቀን ጅማሬ አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ማልዶ ከአፋፉ ላይ አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ያ ኩሩ ገበሬ አአአአአ
ሆ ሲል አረሙን ነቅሎ ድምፁ እያስተጋባ
ለዱር ለእንስሳቱ ቃልኪዳን ሲገባ
እንደመስኩ ቦይ ውሀ ልቤን በዋሽቱ
እየቃኘ ገራው በዓይነ ደግነቱ
ስማኝ አንተው፣ ወትሮም በራስ ተደብቆ
ስማኝ አንተው፣ መች ያስባል ሆድ አርቆ
ስማኝ አንተው፣ ህሊና ነው ክቡር ፀጋ
ስማኝ አንተው፣ አለኝ ታረቅ ከራስህጋ ስማኝ …
ስማኝ አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ ማንነትህን ዞረህ ቃኝ
ስማኝ አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ ማንነትክን ዞረ ቃኝ
           …………
የመስኩ ትንፋሽ ያ ዜመኛ
ቅኔ ዘራፊው ደግ እረኛ
ወዲያ ሲል ልቤ ማዶ ማዶ
እየታዘበኝ ከብት አግዶ
ኧረግ አንተው ብርቱ ዓይናማ
አለኝ  ድንገት ስማኝ እማ ስማኝ ስማኝ ስማኝ
በአእዋፍ ድምፀ ንጋት አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ውብ ዝማሬ ቃና አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ደግሞ ድርሳኑ ላይ አ አሀሀ አሀሀ አሀሀ አሀሀ
ፀሎተ ምስጋና አአአአአ
በትንሽ የወንዝ አለት ሞፈር እየሳለ
ሲያባብል በፉጨት ና በሬው እያለ
ለሆድህ ፍሬ ክንዱ ዘርቶ እሸት ለማብቀል
አይታይህም ወይ ከአፈሩ ሲታገል
ስማኝ አንተው፣ ወትሮም በራስ ተደብቆ
ስማኝ አንተው፣ መች ያስባል ሆድ አርቆ
ስማኝ አንተው፣ ህሊና ነው ክብር ፀጋ
ስማኝ አንተው፣ አለኝ ታረቅ ከራስህጋ ስማኝ…
ስማኝ አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ ማንነትክን ዞረህ ቃኝ
ስማኝ አለኝ ዜማው አንት ሞኝ
ስማኝ ማንነትክን ዞረህ ቃኝ ስማኝ ስማኝ ስማኝ
Written by: Anteneh Worash, Wondwosen Yihub

Loading...