album cover
Tigste
album cover
Tigste은(는) {albumName} 앨범에 수록된 곡으로 2009년 3월 6일일에 AM MUSIC PRODUCTION에서 발매되었습니다.Minew Shoa!
2009년 3월 6일
라벨AM MUSIC PRODUCTION
언어English
멜로디에 강한 음악
어쿠스틱 악기 중심
발랑스
춤추기 좋은 음악
에너지

가사

ከልጅነት እድሜ እስካሁኗ ህይወቴ
ፍቅርሽ ነው ፍቅርሽ ነው ሃይማኖቴ እምነቴ
ገና ደግሞ ገና አመልክሻለሁ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ስቆም እንዳልኮራ ስወድቅ እንዳልፈራ
ዝሆንን አክብሬ በወፊቷ እንዳልኮራ
አስተምረሽኛል የዓለምን ከንቱነት እያልሽ ዓለም ተራ!
ቀንና ለሊቴ ንጋቴ ምሽቴ ተዘርዝሮ ቢታይ ወራት አመታቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ቀንና ለሊቴ ወራት አመታቴ ተዘርዝሮ ቢታይ ንጋቴ ምሽቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ከልጅነት እድሜ እስካሁኗ ህይወቴ
ፍቅርሽ ነው ፍቅርሽ ነው ሃይማኖቴ እምነቴ
ገና ደግሞ ገና አመልክሻለሁ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ስፈጥን ረጋ በል ረጋ ስል በል ፍጠን
ስጠፋ ተመለስ እያልሽኝ ቀን በቀን
አሳይተሽኛል ህይወትን ያለ አጥር ፍቅርን ያለ ወሰን
ቀንና ለሊቴ ንጋቴ ምሽቴ ተዘርዝሮ ቢታይ ወራት አመታቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ቀንና ለሊቴ ንጋቴ ምሽቴ ተዘርዝሮ ቢታይ ወራት አመታቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ገና አመልክሻለሁ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
ገና አመልክሻለሁ ነፍሴ ነሽ ትዕግስቴ
Written by: Abdu Kahssay
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...