가사

ውለታሽ አለብኝ ልከዳሽ አልወድም ስምሽን በቁም ነገር አነሳለሁ የትም የክፉ ቀን ጓዴ ብልሽ እወዳለው ብድር መላሽ ያድርገኝ አመሰግናለው ያን ጊዜ ስቸገር ጨለማ ሲውጠኝ ወዳጄን ጠላቴን መለየት ሲያቅተኝ ፈጥነሽ ደረሽልኝ ፍቅር አልጎደለብሽ የክፉ ቀን ጓዴ መመስገን አለብሽ የውለታ ጉዳይ ውለታ ነው መልሱ የተሳካ ለታ ከቀኑ ሲደርሱ ይሙላልኝ በማለት ከርሚያለው ስመኝ ብድር ለመመለስ እላለው ቀን ይስጠኝ ወዳጄ እንደምን ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ አመሰግናለው ውለታሽ አለብኝ ልከዳሽ አልወድም ስምሽን በቁም ነገር አነሳለሁ የትም የክፉ ቀን ጓዴ ብልሽ እወዳለው ብድር መላሽ ያድርገኝ አመሰግናለው ኩምነገር ደግነት መልካም ምግባሮችሽ ከሀውልት ጠንክረው ቆመው ሲያበሩልሽ ከልቤ መሀደር ስፍራም ሳይጠባቸው በክብር ተቀምጠው አሉ ህያው ናቸው ከውለታም ደግሞ ውለታ ነው እንጂ ችግር ሲያፋጥጠኝ ስትሆኚኝ ቀኝ እጅ የደግነት ንግስት ብልሽ ምን ያንስሻል የዘላለም ሀውልት ከልቤ ተክለሻል ወዳጄ እንደምን ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ አመሰግናለው ወዳጄ እንደምን ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ መመኪያዬ እንዴት ነሽ ወዳጄ እንደምን ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ መመኪያዬ እንዴት ነሽ ወዳጄ እንደምን ነሽ አለኝታዬ እንዴት ነሽ የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ መመኪያዬ እንዴት ነሽ ወዳጄ እንደምን ነሽ
Writer(s): Neway Debebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out