Letra

ሰው መሠረቱ መቼ ይለያያል በአንድ አምሳል ተፈጥሮ አንድ ሆኖ ይታያል ሃብትን የታደላት ትልቅ ሰው ይባላል ያጣም ድህነቱን አምኖ ይቀበላል ያለለትን ሊኖር እድሜውን ሲገፋ ከቶ በህይወቱ ማነው የማይለፋ ደስታና መከራ ማግኘቱ ማጣቱ ሁሉም በየተራ አይቀርም መምጣቱ ተፈራርቆ የሚኖር በየራሱ ጊዜ በየራሱ ጊዜ የአንድ ቦይ ውሃ ነው ተድላና ትካዜ ተድላና ትካዜ ውጣ ውረድ ባለው የህይወት መሰላል የህይወት መሰላል የዚህች ዓለም ነገር በዚህ ይመሰላል በዚህ ይመሰላል ሰው መሠረቱ መቼ ይለያያል በአንድ አምሳል ተፈጥሮ አንድ ሆኖ ይታያል ሃብትን የታደላት ትልቅ ሰው ይባላል ያጣም ድህነቱን አምኖ ይቀበላል የሆነለት ወጥቶ ያቃተውም ወርዶ ሁሉም ይቀበላል የኑሮን ተፈርዶ ህይወት በደረጃ ሰው ይነጣጥላል አንዱን ላይ አድርጎ አንዱን ታች ይጥላል የሌለው ዳቦ አጥቶ ያለው ሙክት ሲያንሰው ያለው ሙክት ሲያንሰው ላገኘው ሲጨምር ካጣ እየቀነሰው ካጣ እየቀነሰው የእድሜ መጨረሻ ሲመጣ ሰዓቱ ሲመጣ ሰዓቱ ሞቱ ግን አንድ ናት ቢለይም ህይወቱ ቢለይም ህይወቱ ሰው መሠረቱ መቼ ይለያያል በአንድ አምሳል ተፈጥሮ አንድ ሆኖ ይታያል ሃብትን የታደላት ትልቅ ሰው ይባላል ያጣም ድህነቱን አምኖ ይቀበላል ሊቁ ዘመን እንጂ አይደለም ጠቢብ የሚሆን ምን አለ እንደ ሰው ሃሳብ በዓለም ላይ ጊዜ ነው ሁሉን የሚያደርገው ተስካሩን ያወጣል ሰውስ በሰረገው የበላይ በበታች ይገፋል ከወንበር ይገፋል ከወንበር በዓለም ምን ይኖራል ወትሮስ እንደነበር ወትሮስ እንደነበር ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ ይበላል ደብተራ ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ የትንሾች ተራ የበላይ በበታች ይገፋል ከወንበር ይገፋል ከወንበር በዓለም ምን ይኖራል ወትሮስ እንደነበር ወትሮስ እንደነበር ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ ይበላል ደብተራ ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ የትንሾች ተራ ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ ይበላል ደብተራ ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ የትንሾች ተራ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out