Letra

አመሰግናለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና ሁሉን ፡ ይሁን ፡ ያለ ፡ ውብ ፡ አሮጐ ፡ የሰራው ፡ እርሱ ፡ ነውና ብቻውን ፡ የሚኖር ፡ በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ ሰው ፡ በማይቀርበው የፍጥረት ፡ መሰረት ፡ ተቆጣጣሪ ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው (፪x) ላመስግነው ፡ ቆሜ ፡ እንደገና ፡ ጥበብ ፡ ኃይልም ፡ የእርሱ ፡ ነውና ከንፈሮቼ ፡ ለእርሱ ፡ ይዘምሩ ፡ እስትንፋሴም ፡ ይሁን ፡ ለክብሩ (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከቦኝ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ መቆሜ ፡ አሄ ትንፋሼን ፡ መንገዴን ፡ በእጆቹ ፡ የያዘው ፡ ሆኖልኝ ፡ አቅሜ ፡ ሄሄ ወራት ፡ ተቆጠሩ ፡ አመታት ፡ አለፉ ፡ ዛሬም ፡ ዘምራለሁ ፡ አሄ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ስለፈቀደልኝ ፡ አመሰግናለሁ ፡ ሆሆ አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x) አመጸኛው ፡ ጠላት ፡ ከሚወረውረው ፡ ጦር ፡ እያስመለጠኝ ፡ አሄ ቀስት ፡ እየሰበረ ፡ እሳት ፡ እያጠፋ ፡ በእጁ ፡ እየከለለኝ ፡ ሆሆ ከአቻምናን ፡ አልፌ ፡ አምናንም ፡ አልፌ ፡ ኢኸው ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ አሄ ቀሪውን ፡ ዘመኔን ፡ እንዲባርክልኝ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ ፡ ሆሆ አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x) የእግዚአብሔር ፡ ደግነት ፡ በምን ፡ ይመዘናል ፡ መለኪያስ ፡ አለው ፡ ዎይ ፡ አሄ ከጨለማው ፡ ዓለም ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ ታድጐኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ ሆሆ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የነፍሴ ፡ መድሃኒት ፡ የዓለሙ ፡ ቤዛ ፡ አሄ በእርሱ ፡ ተመርጬ ፡ በደሙ ፡ ነጽቼ ፡ ቀረልኝ ፡ አበሳ ፡ ሆሆ አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x) "እንግዲስ ፡ እርምጃዬ ፡ የማስተዋል ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ የሚከብርበት የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮዬን ፡ በትዕግሥት ፡ ሮጬ ፡ የምጨርስበት በቀንም ፡ በማታም ፡ አምላኬን ፡ የመፍራት ፡ ጥበብ ፡ ይሁንልኝ የሮጥኩት ፡ ሩጫ ፡ በእሳት ፡ ስፈተን ፡ አይቃጠልብኝ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ በዐይኔ ፡ እስካየው ፡ ድረስ ፡ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ልገዛ ፡ በውነት ፡ ልስገድለት ውዱ ፡ ጌታ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ (፪x) ከፍ ፡ ይበል ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ይንገሥ"
Writer(s): Samuel Alemu, Daniel Amdemichael Amdemariam Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out