Видео
Лучшие песни Daniel Amdemichael
Создатели
ИСПОЛНИТЕЛИ
Daniel Amdemichael Amdemariam
Исполнитель
МУЗЫКА И СЛОВА
Daniel Amdemichael Amdemariam
Автор песен
Слова
ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነ
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ይጠብቀኛል
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ህይወት ሆኖኛል
°°°
አምላክ ያዘጋጀው ኢየሱስ የዓለም ቤዛ የዓለም መድኃኒት
እንዳልነዋወጥ ወጀቡ እንዳይጥለኝ ሆኖኝ መሠረት
መንፈሱ ሞልቶኛል በቤቱ ተክሎኛል
ዓለም የማይሰጠውን ሰላም ሰቶኛል
መንፈሱ ሞልቶኛል በቤቱ ተክሎኛል
ዓለም የማይሰጠውን ሰላም ሰቶኛል
ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነ
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ይጠብቀኛል
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ህይወት ሆኖኛል
°°°
የላቀ ደስታ ዓለምን የሚያስንቅ ሰላመ ሰማይ
በቃሉ ላመኑ ከጌታ ተሰጥቷል ከሱ ዘንድ ከላይ
እኔም ይህን ደስታ እረፍት አግኝቻለሁ
እየተደነኩኝ አመልከዋለሁ
እኔም ይህን ደስታ እረፍት አግኝቻለሁ
እየተደነኩኝ አመልከዋለሁ
°°°
እግዚአብሔር በቃሉ በመንፈሱ ሙላት የባረካችሁ
በደስታ እናምልከው እልልታው ይሰማ ይውጣ ድምፃችሁ
ጌታችን ይመስገን ይደርደር በገና
የሰላሙ ንጉስ እሱ ነውና
ጌታችን ይመስገን ይደርደር በገና
የሰላሙ ንጉስ ኢየሱስ ነውና
ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነ
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ይጠብቀኛል
ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለእኔ ነው ህይወት ሆኖኛል
Writer(s): Daniel Amdemariam
Lyrics powered by www.musixmatch.com