Создатели

МУЗЫКА И СЛОВА
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Автор песен
Anteneh Aklilu
Anteneh Aklilu
Автор песен
ПРОДЮСЕРЫ И ЗВУКОРЕЖИССЕРЫ
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Продюсер
Kirubel Tesfaye
Kirubel Tesfaye
Миксинг-инженер
Melaku Sisay
Melaku Sisay
Продюсер

Слова

የፍቅርሽን እሳት ከልቤ ቀብሬ
እኔስ ሄጄ ነበር ካድማስ ተሻግሬ
ከራኩበት ቦታ
ፍቅርሽ ጠራኝ በድሜዬ እኩሌታ
ተለየሁሽ ብዬ እስከመጨረሻ
ተመልሶ ጠራኝ የመውደድሽ ግርሻ
በናፍቆትሽ በትር ልቤን እየቀጣ
ፍቅርሽ ይዞኝ መጣ
በዘመን በርቀት ያልከሰመ ፍቅር
እንደአዲስ ሲጠራኝ እንዴት ብዬ ልቅር
ተስፋ ያጎበዛት ነፍሴን አንጠልጥዬ
ክንፍ አብቅዬ መጣሁ ባዛኝ ቀልቤን ጥዬ
ደረትሽ ላይ ውዬ መውደድሽን ባላገኝ
ፍቅርሽ አምጥቶኛል እንዳረገ ያርገኝ
ይኸው (ከርሞ
ፍቅርሽ ጠራኝ ደግሞ
ወደ ልጅነቴ
ወደ ጥንቱ ቤቴ።
ይኸው ከርሞ
ፍቅርሽ ጠራኝ ደግሞ
የፍቅርሽን እሳት ከልቤ ቀብሬ
እኔስ ሄጄ ነበር ካድማስ ተሻግሬ
ከራኩበት ቦታ
ፍቅርሽ ጠራኝ በድሜዬ እኩሌታ
ጊዜው ደርሶ ዛሬ፣ ደጅሽ የመለሠኝ
የተራብኩት ፍቅርሽ፣ በእቅፉም ባይክሰኝ
ዘመን ይለፍብኝ፣ ልብሽን ሳንኳኳ
ቢዘነጋኝ እንኳ
መውደድ ስታበስርሽ፣ ነፍሴ በመለከት
አሜን ባትይ አንቺ፣ የፍቅርን በረከት
መአዛሽ ካለበት፣ ከአንባሽ ተገኝቼ
ሳዜም እኖራለሁ፣ ቃልሽን ተቀኝቼ።
አውቀዋለሁና፣ የናፍቆትሽን አቅም
ዳግም ለሰቀቀን፣ (እግሬን አላርቅም)*2።
ይኸው ከርሞ
ፍቅርሽ ጠራኝ ደግሞ
ወደ ልጅነቴ
ወደ ጥንቱ ቤቴ
ይኸው ከርሞ
ፍቅርሽ ጠራኝ ደግሞ
Written by: Anteneh Aklilu, Michael Belayneh, Solomon Sahele
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...