Слова

የዉበቷ ግርማ ከሩቅ የሚስበው ዳሌ ተረከዟ ሽንጧ የረቀቀው አይኗ እንደጦረኛ የሚያስበረግገው ደረቷ እንደጋሻ ደርሶ ሰፋ ያለው ጡቷ እንደአራስ ነብር አትንኩኝ የሚለው አንገቷ እንደሰጎን ተመዞ የወጣው አፏ እንደህጻን ልጅ የሚርበተበተው እንደቀትር እባብ ፍቅሯ የልቤን አዳራሽ እልፍኟ ታድርገው ካንጀቴ ውስጥ ገብታ ልቤን አንድ ለአንድ መታገል ሲያቅተው ሰው ሁሉ አንቺ ሰው በሰው ላይ ትጥያለሽ አሉ ኦይ ሰውነቷ እንደው ሰውነቷ አንቺ ካለሽበት ከቆምሽበት ምድር አንቺ ካለሽበት ከቆምሽበት ምድር መነኩሴው ከገዳም ጎሽ ይወጣል ከዱር አንበሳን በጡቻ እለው የነበረ ዝሆንን በጡቻ እለው የነበረ ነብርን በጡቻ እለው የነበረ እባብ ጭንቅላቱን እለው የነበረ ምነው ካንቺ ሲደርስ ልቤ ደነበረ ኣይ ሰውነትሽ እንዲያው ሰውነቷ ምነው እኔ ምነው እኔ (×3) ቻዪኝ እንዳመሌ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ (×3) አንጀቴና ሆዴ ተጣልተውብኝ አንተም አንተም ተው ብዬ እንዳልለው አንጀቴም አንጀቴ ሆዴም ሆዴ ነው ለማን እፈርዳለው ፍርድ አያውቅም ሰው ኦይ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ አንቺ አኩራፊ ሆነሽ እኔ ሆደ ባሻ አንቺ አኩራፊ ሆነሽ እኔ ሆደ ባሻ በቃ ተለያየን እስከመጨረሻ አበባው ፈነዳ ቡቃያው ደረሰ ፍቅሬ. ... ምነው ደፈረሰ ኣይ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ የኔና ያንቺ ብቻ ፍቅራችን ከሰመ የመለየት ጉጉት በኛ ላይ ዘመመ የመለየት ጉጉት በኛ ላይ ዘመመ ኦይ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ ሰውነቷ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ ኦይ ሰውነቷ እንዲያው ሰውነቷ ምነው እኔ ምነው እኔ ምነው እኔ ቻዪኝ እንዳመሌ ምነው እኔ ምነው እኔ ምነው እኔ ቻዪኝ እንዳመሌ
Writer(s): Traditional Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out