album cover
Amen
9,217
World
Amen was released on May 2, 2017 by Teddy Afro as a part of the album Ethiopia
album cover
Release DateMay 2, 2017
LabelTeddy Afro
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM114

Credits

PERFORMING ARTISTS
Teddy Afro
Teddy Afro
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Teddy Afro
Teddy Afro
Songwriter

Lyrics

ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው
ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው
ጋልቦ በገራው ፈረሰ ርቆ ተጓዥ ለጉዳይ
እንዴት ይጥላል ልቡን በድንገት ከአደባባይ
ወይ ካደረግሽው ማርከሽ የፍቅርሽ ሟች ተረኛ
በቃ አሳርፊው ልቤን አታስጨንቂኝ ተይኛ
አሀ-አሀ-አሀ፣ አሀ-አሀ-አሀ ሀይ
እርፍ ይበል ልቤም ቁርጡን አውቆ፣ ቁርጡን አውቆ
እንዴት ይችላል ታዲያ እንዲህ ተጨንቆ፣ እንዲህ ተጨንቆ
የወደደ ታሞ ባይዝ አልጋ፣ ባይዝ አልጋ
ቆሞ ሲሔድ ሁሌም ከራሱጋ፣ እያወጋ
እንደድንገት ልቤ ድንግጦ
ጥሎኝ ሔደ ከኔ አንቺን መርጦ
የደነገጠው ልቤን ወስደሽው
በይ ንገሪኝ የት አደረግሽው
ይሔኔ ልቤን ጥለሽ ይሆናል
በዚህ ግዜ ማን ይታመናል
የያዘኝ ፍቅርሽ የረታው አቅሜን
ባንቺም ደርሶ ምነው ባልኩ አሜን
አሜን አሜን (አሜን)፣ ኸረ አሜን አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ ኸረ አሜን አሜን (አሜን)
ልቤን (ልቤን) እንዳጣው አቅሜን (አቅሜን)
ባልኩኝ (አሜን)፣ ፍቅር ይዞሽ አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ አሜን አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ አሜን አሜን (አሜን)
ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው
ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው
እንዴት ሳያጉረመርም ዝናብ ይጥላል ሰማይ
ድንገት አራሰው ልቤን ውበትሽ መስሎ ፀሀይ
ሀሳብ ቀላቅሎ ሲጥል እኔስ ብርዱ ገደለኝ
ምነው ወይ አዝኖ ልብሽ ከፍቅርሽ ቢያስጠልለኝ
አሀ-አሀ-አሀ፣ አሀ ተይ
እትት ሲል ጐኔም አንችን ናፍቆ፣ አንችን ናፍቆ
እንዴት ይችላል ታዲያ እንዲ ተጨንቆ፣ እንዲ ተጨንቆ
ዘምቦ በኔ ፍቅርሽ እስኪያባራ፣ እስኪያባራ
ምነው ቢኖር ልቤ ካንቺ ጋራ፣ ባንድ ጣራ
እንቺ ምክር ካንቺ ባላውቅም
ሀይለኛ ነው ፍቅር አይናቅም
በዚህ ምድር የፈሩት ደርሶ
ስንት አይተናል የናቁት ወርሶ
የናቁት ወርሶ ብድር ሲመልስ
ያስጨንቃል መቼም አያድርስ
እኔ በፍቅርሽ እንዳጣው አቅሜን
ባንቺም ደርሶ ምነው ባልኩ አሜን
አሜን አሜን (አሜን)፣ ኸረ አሜን አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ ኸረ አሜን አሜን (አሜን)
ልቤን (ልቤን) እንዳጣው አቅሜን (አቅሜን)
ባልኩኝ (አሜን)፣ ፍቅር ይዞሽ አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ አሜን አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)፣ አሜን አሜን (አሜን)
አሜን አሜን (አሜን)
Written by: Teddy Afro
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...