album cover
Nat Baro
album cover
Nat Baro was released on May 2, 2017 by Teddy Afro as a part of the album Ethiopia
May 2, 2017
LabelTeddy Afro
BPM84
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ጥቁሯ ወርቅ ቀጥ እንደ ሸምበቆ
አኳኋኗ በአታሞ ምት ረቆ
ፍቅር ሲሞቅ እሳት ነዶ ማታ
ውበት አየሁ ዳንኪራ ሲመታ
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ፣ ናት የባሮ!
ቶም ሰርታ በዣንጥላው ብረት
በጨረቃ ፍቅርን ያዜምንበት
የታንኳው ላይ የወንዙ ሽርሽር
እረፍት አጣው ትዝ ባለኝ ቁጥር
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ፣ ናት የባሮ!
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
መሸት ሲል ጀምበር አዘቅዝቆ
ቀዩን ሰማይ ውሃው አንፀባርቆ
እያየኋት በጨረቃ መብራት
አማረኝ የታንኳ ላይ እራት
ጉድ አረገኝ በውበት ሳር አስሮ፣ አዬ ባሮ
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ይሄ ልቤ የሆነብኝ ምነው?
ሀሳቤ ሁሌ ከአዊሊ ነው
ልያት እንጂ ወይ ሄጄ ዳግመኛ
ባደርጋት የሁሌ ጓደኛ
ዓሳ ሆኖ ልኮኝ እንጀራዬ
ከአዲስ አበባው የትውልድ አምባዬ
ተመለስኩኝ በፍቅሯ ተይዤ
የሸገር ልጅ ባዶ ቅርጫት ይዤ
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አገነ ገቲያ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አነ ሚየጎ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አጀሎዬ!)
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ፣ አሳ አጠምድ ብሎ
ናት ባሮ፣ ዘርግቶት መረቡን
ናት ባሮ፣ እንዴት ለቆንጆ ሴት
ናት ባሮ፣ ሰው ይጥላል ልቡን
ናት ባሮ፣ ዓይኔ እሷ ላይ ቀርቶ
ናት ባሮ፣ ዓሳ አጣሁ ለእራቴ
ናት ባሮ፣ ባዶ ቅርጫት ይዤ
ናት ባሮ፣ ተመለስኩኝ ቤቴ
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ፣ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አገነ ገቲያ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አነ ሚየጎ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አጀሎዬ!)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (ጋምቤላ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አገነ ገቲያ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ (አነ ሚየጎ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ...
Written by: Teddy Afro
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...