album cover
Basiresagn
2,753
World
Basiresagn was released on April 12, 2004 by Nahom Records Inc as a part of the album Best Singles of 2003 (Nahom Favorite, Vol. 3)
album cover
Release DateApril 12, 2004
LabelNahom Records Inc
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM90

Credits

PERFORMING ARTISTS
Bitsat Siyuom
Bitsat Siyuom
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Bitsat Siyuom
Bitsat Siyuom
Songwriter
Bisat Seyoum
Bisat Seyoum
Songwriter

Lyrics

በተሳልኩት ስለት ካልወጣሁ ከማፍቀር
ከማፍቀር ከማፍቀር እኔማ ከማፍቀር
ስረሳ ካላየሁ ከሃሳቤ ስትቀር
ስትቀር ስትቀር የኔ ዓለም ስትቀር
ምን ብዬ አነግሣለሁ ከእንግዲህ ታቦቱን
ታቦቱን ታቦቱን እኔማ ታቦቱን
ባንተ ለመጨከን ካልሰጠኝ ሐሞቱን
ሐሞቱን ሐሞቱን ጌታዬ ሐሞቱን
በሆነለት በሆነለት
ልቤ መርሳት በሆነለት
በሆነለት በሆነለት
አንተን መተው በሆነለት
ድንኳን ቢቸግረኝ ባጣ እንኳን ማደሪያ
አላውቅም ቀርቼ እኔ ጽዮን ማርያም
በጠዋቱ ገዳም ግሸን ተሻግሬ
ምላሽ አልነበረም የልቤን ነግሬ
ዛሬ ካንተ ርቄ ብሳል በነጠላ
ጠፋ ሰሚ ታቦት ወዶ ለሚጠላ
በእንጦጦዋ ብልህ በኪዳነምሕረት
ተወው በእመቤቴ ይሄን ደርሶ መቅረት
ተወው በእመቤቴ ይሄን ደርሶ መቅረት
ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ
በተሳልኩት ስለት ካልወጣሁ ከማፍቀር
ከማፍቀር ከማፍቀር እኔማ ከማፍቀር
ስረሳ ካላየሁ ከሃሳቤ ስትቀር
ስትቀር ስትቀር የኔ ዓለም ስትቀር
ምን ብዬ አነግሣለሁ ከእንግዲህ ታቦቱን
ታቦቱን ታቦቱን እኔማ ታቦቱን
ባንተ ለመጨከን ካልሰጠኝ ሐሞቱን
ሐሞቱን ሐሞቱን ጌታዬ ሐሞቱን
በሆነለት በሆነለት
ልቤ መርሳት በሆነለት
በሆነለት በሆነለት
አንተን መተው በሆነለት
በአቦ በሥላሴ በገብርኤል ብዬ
አልሰማ ብትለኝ ተጓዝኩ እኔስ ጥዬ
ለነፍሴ ለማደር ምንኩስናን ብሻ
በእኔ መንኚ አለኝ ፍቅርህ እንደ ዋሻ
ዓለም በቃኝ ብዬ ገና ቆቤን ሳልጭን
ዐይኖችህ ይሉኛል እገዳምሽ አምጪን
እነሱን አልመን አይተው ያልጠገቡ
ለነፍስ ያድራሉ ወይ ከገዳም ቢገቡ
ለነፍስ ያድራሉ ወይ ከገዳም ቢገቡ
አንተማ ላመልህ እበተስኪያኑ ውለህ
ትሳላለህ አሉኝ ጥላ አመጣ ብለህ
ጧፉ ሲወረወር እጣን ሲዘረገፍ
ምነው ባላሳየኝ እኔስ ያንተን መርገፍ
ምነው ባላሳየኝ እኔስ ያንተን መርገፍ
ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ
ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ
ባስረሳ ባስረሳኝ
ባስረሳ ባስረሳኝ
ባስረሳ ባስረሳኝ
ባስረሳ ባስረሳኝ
Written by: Bisat Seyoum
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...