Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Daniel Amdemichael Amdemariam
Daniel Amdemichael Amdemariam
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Daniel Amdemichael Amdemariam
Daniel Amdemichael Amdemariam
Songwriter

Lyrics

አዝ፦ ምህረቱ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ለጌታዬ ፡ መዝሙር ፡ ባመጣ ሊያነቃቃኝ ፡ የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ሊዳስሰኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ወጣ እዚህ ፡ አይደርስም ፡ ዋጋም ፡ የለውም ፡ በሰዎች ፡ አፍ ፡ የተባለን ፡ ሰው አይገርምም ፡ ዎይ ፡ በቸርነቱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳው አይገርምም ፡ ዎይ (፬x) አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x) እንደገባኝ ፡ መጠን ፡ እንደተረዳሁት አምላኬን ፡ ባመልከው ፡ ማነው ፡ ቅር ፡ የሚሰኝ (፪x) ከልብ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ ኧረስ ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እራቁቴን ፡ ባመልከው ሜልኮል ፡ አይደለችም ፡ የእኔ ፡ ዳኛ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)[1] አዝ፦ ምህረቱ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ለጌታዬ ፡ መዝሙር ፡ ባመጣ ሊያነቃቃኝ ፡ የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ሊዳስሰኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ወጣ እዚህ ፡ አይደርስም ፡ ዋጋም ፡ የለውም ፡ በሰዎች ፡ አፍ ፡ የተባለን ፡ ሰው አይገርምም ፡ ዎይ ፡ በቸርነቱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳው አይገርምም ፡ ዎይ (፬x) አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x) እኔ ፡ አውቀው ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ ያደረገልኝን ከጨለማ ፡ አውጥቶ ፡ ቀን ፡ ያወጣልኝን (፪x) የምን ፡ ቁጠባ ፡ ነው ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ዝምታ ምሥጋና ፡ ይድረሰው ፡ ለሠራዊት ፡ ጌታ ለሠራዊት ፡ ጌታ (፪x) አይገርምም ፡ ዎይ (፬x) አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x)
Writer(s): Samuel Alemu, Daniel Amdemichael Amdemariam Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out