album cover
Eyesus
album cover
Eyesus was released on September 12, 2019 by Ephrem Alemu as a part of the album Jesus
AlbumJesus
September 12, 2019
LabelEphrem Alemu
BPM
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

ወዳጄ ኢየሱስ የቅርቤ ነህ
ዘመን ሲከፋ ትደርሳለህ
አባቴ ኢየሱስ የግሌ ነህ
ኑሮ ሲጨልም ትመጣለህ
ከዛ ድቅድቅ ምድረ በዳ
ያወጣኸኝ ሳልጐዳ
ወጀቡንም ያሳለፍከኝ
አንተ እኮ ነህ የታደከኝ
አይይ አባት ሆንክልኝ
የልቤ ወዳጅ ብዬ ያልኩት
ሚስጥሬንም የነገርኩት
ቀኑ ደርሶ ቢከዳኝም
ጊዜው መጥቶ ቢርቀኝም
አይይ አንተ አትርቀኝም
እንኳን ያንተ ሆንኩ እንኳን ያዝከኝ
የአንተ ባልሆን ኖሮ ሟች ነበርኩኝ
ኸረ እንኳን ያንተ ሆንኩ እንኳን ያዝከኝ
የአንተ ባልሆን ኖሮ ሟች ነበርኩኝ
ወዳጄ ኢየሱስ የቅርቤ ነህ
ዘመን ሲከፋ ትደርሳለህ
አባቴ ኢየሱስ የግሌ ነህ
ኑሮ ሲጨልም ትመጣለህ
እውነተኛ እረኛዬ
የዘላለም ጓደኛዬ
ኢየሱስ ነህ የናዝሬቱ
እወድሃለሁ በየለቱ
አይይ በዝቷል ምህረቱ
በሰዎች አይን የማይሞላ
በመንደሩ የተጠላ
ዛሬ ክብር ቢበዛለት
ምንጩ አንተ ነህ ክበርለት
አይይ አባት ሆንክለት
እንኳን ያንተ ሆንኩ እንኳን ያዝከኝ
የአንተ ባልሆን ኖሮ ሟች ነበርኩኝ
ኸረ እንኳን ያንተ ሆንኩ እንኳን ያዝከኝ
የአንተ ባልሆን ኖሮ ሟች ነበርኩኝ
ወዳጄ ኢየሱስ የቅርቤ ነህ
ዘመን ሲከፋ ትደርሳለህ
አባቴ ኢየሱስ የግሌ ነህ
ኑሮ ሲጨልም ትመጣለህ
Written by: Ephrem Alemu
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...