album cover
Sema
153
Reggae
Sema was released on February 8, 2019 by Online Communications PLC as a part of the album Yohana
album cover
AlbumYohana
Release DateFebruary 8, 2019
LabelOnline Communications PLC
LanguageEnglish
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM87

Music Video

Music Video

Credits

Lyrics

ወዴት ትሸሻለህ? ወዴት ይሸሻል?
ወዴት ትሮጣለህ? የት ይደረሳል?
ሸሽቶ ከራስ፣ ሮጦ ከራስ
ስማ . . . . . . . . . . . . . . . . . ስማ
በሰፊ መንገድ ጋጋታ አጀቡ አይደለም ህይወት
መኖር ነው በራስ በጠባብ ውስጥን ያከበሩለት
ቢሆንም ከባድ መንገዱ መኖርም ይኸው ነው ግዱ
ቢሆንም ከባድ መንገዱ መኖርም ይኸው ነው ግዱ
በመከተል ብትጠፋ ድቅድቅ ጨለማ መሀል
መመለሻው ቢሆን ድፍን ነብስ ቢጨነቅ በሃይል
ማንን ነው ምትጠይቀው
ማንን ነው ምትጠይቀው
በግልፅ ቢታይ ውስጥህ ጊዜ ካለፈ በኋላ
ቁጭት ንዴት ፍርሃት ፀፀት ቢያሳጣህ መላ
ማንን ነው ምትጠይቀው
ማንን ነው ምትጠይቀው
እንደ ራስ ይሻላል እንደ ራስ
እንደ ራስ ይሻላል እንደ ራስ
ስማ... ብታስብ አንድ ላይ
የለም ከቶ ለራስህ ሆኖ እንዳንተ ሚያይ
ስማ... ከጎንህ ኖሮ
የለም ከቶ የሚያይ ላንተ ከቆምክበት ቆሞ
በሰፊ መንገድ ጋጋ.ታ ህይወት አይደለም ጅረት
መስመር ነው የራስን ጠባብ ውስጥን ያከበሩለት
ቢሆንም ከባድ መንገዱ መኖርም ይኸው ነው ግዱ
ቢሆንም ከባድ መንገዱ መኖርም ይኸው ነው ግዱ
መኖር ህይወት ሌላው ማይገባው
ካመንክበት አንተ አይዞህ ሰላም ነው ሰላም ነው
ከታየህ እውነት ነብስ ሚበላው
አያሳስብህ አይዞህ ሰላም ነው ሰላም ነው
እንደራስ ይሻላል እንደራስ
እንደራስ ይሻላል እንደ ራስ
አይ ስማ... ስማ...
Written by: Marven, Yohana
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...