Lyrics

ከባድ ነው መኖር ያላንቺ ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋር የረዘመ ሌት ሲሉ አይነጋም ደግም ያጠረ ቀን አንሶ አይበቃም ፍቅርሽ በመናው ልቤ ገብቶ መስኮት ይከፍታል በሩን ዘግቶ ለመሄደሰ ማሰብ አንቺን ጥሎ ከባድ ሆነብኝ ቀላል መስሎ ሳዝን ለልቧ ለወደደኝ መሣቅ አይድል ወይ የከበደኝ ባንድ የኖሩለት ዉሀና እሳት ከባድ አይድል ወይ ቀላል ማሣት ብቻዬን ልኑር ብል ያላንቺ ኦና ነው ቤቴም አይመቺ ከባድ ነው መኖር ያላንቺ ልቤን አልኩና በሷው እርጋ ብታገስ ሌቱም እሥኪነጋ ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋ ከባድ ከባድ ነው መኖር ያላንቺ ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋር ነው እንዴ ያለሤት እራሱ ሲያጥር አምስት የሌለው ሀምሣ ቁጥር ነጭ ያለ ጥቁር መች ይፈካል ሣይኖር ጨለማ እንዴት ይነጋል ድሥት ያለ ክዳን ላይሆን እቃ ምንም አይቀናኝ ተውኩሽ በቃ አስራኝ ከቅርቧ ግራና ቀኝ መራቅ አይደል ወይ የከበደኝ ወተት ቢታገስ መቻል አውቆ ይሆናል ቅቤ ተነቅንቆ ብቻዬን ልኑር ብል ያላንቺ ኦና ነው ቤቴም አይመቺ ከባድ ነው መኖር ያላንቺ ልቤን አልኩና በሷው እርጋ ብታገስ ሌቱም እሥኪነጋ ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋ ከባድ the end
Writer(s): Samuel Alemu, Tewodros Kasshun Germamo Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out