album cover
Amesgnalehu
141
Hip-Hop/Rap
Amesgnalehu was released on May 27, 2022 by Birrz Studio as a part of the album Lewt
album cover
AlbumLewt
Release DateMay 27, 2022
LabelBirrz Studio
LanguageEnglish
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM82

Credits

COMPOSITION & LYRICS
Kirubel Bacha
Kirubel Bacha
Songwriter
SAMUEL TEFERI
SAMUEL TEFERI
Songwriter

Lyrics

እንባሽን አልየው እማ
እናትነት ትዕግስት መስዕዋትነት
የእውነተኛ ፍቅር ጥጉ ሚታይበት
ስለ እናት ተገልፆ አያልቅም ኧረ በኔ አንደበት
ለልጆቹዋ ያላት ርህራሄ ስስት
ምትክ የላት እናትስ እናት ናት
በጋ ሆነ ክረምት ብርሀን ሆነ ለሊት
በመከራ ችግር በሀዘን ሲመታ
ታበረታኛለች ቃልሽ ልቤ ገብታ
ስወድቅ የምትይኝ ተስፋ አትቁረጥ በርታ
የኔ ይቅር አንተ ኑር አንተ ነህ የኔ ደስታ
አለም ስታስከፋኝ በህይወት ስከሰስ
ካሰብኩት ካለምኩት ሲያቅተኝ መድረስ
ስብርብር አንክትክት አላማዬ ሲወድቅ
አለኝ ያልኩት ያ ተስፋ ሲጠፋብኝ ሲርቅ
ባንቺ ህይወት አስተማርሽኝ ትግስትን ልቤ እንዲያውቅ
መከራውን አሳለፍኩት ምክርሽ ሆኖኝ ስንቅ
ሃሳብሽን ባልሞላም ህልሜን ባለልሆንልሽ
ቁም ነገርም ባልደርስበት ማረግ ባላሳይሽ
ሁሉም ቢለዋወጥ አንቺ ለኔ አንድ ነሽ እናቴ አደለሽ ?
ከአውሬው ማምለጫ መደበቂያ ነሽ እማ (መደበቂያዬ ነሽ)
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሸን አልየው እማ እንባሽን አልየው እማ ተይ
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
በፈለግሽኝ ሰዐት ባልደርስልሽ ያኔ
ሙሉ ህይወትሽን ዋጋ ከፍለሽ ለኔ
በቀን ማታ አይ ስንቱን አየሽው
ያን ሁሉ መከራ እናት እንዴት ቻልሽው
የሰው ፊት ጅራፉን ለኔ ተገረፍሽው
በጨለማ ኖረሽ ልቤን ብርሃን ሞላሽው
ጉዞ ጀምሪያለው ብቻ አንቺን አይክፋሽ
መድረሴ አይቀርም እማ ተስፋ አልቆርጥም ጭራሽ
አዎ እማ ላንቺ እጨነቃለው
እንደሆንሽልኝ ልሆን እንከራተታለው
እዚም እዛ ይኸው እሮጣለው
መንገዴ ረዘመ ደስታሽ የኔ አለም ነው
ሰዉ አውሬ ሆኗል እኔ አልችል ብያለው
ምክንያቱም ፍቅርን ካንቺ ተምሪያለው
ርህራሄ ደግነትን ካንቺ ወርሻለው
ግን አላዝንም ዛሬም በልቤ አይሻለው
ይሳካል ሃሳብሽ እማ ፀሎትሽ ዋጋ አለው
ሰላሙን ያብዛልሽ መቼም ክፉሽን አልየው
ሳቅሽ ለኔ እረፍት ደስታሽ ህይወቴ ነው
ከፍዬ አልጨርሰው እማ ውለታሽ ብዙ ነው
ምስጋናዬን ተቀበይኝ እማ እወድሻለው (እማ እወድሻለው)
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሸን አልየው እማ እንባሽን አልየው እማ ተይ
ክፉሸን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
እንባሽን አልየው እማ ተይ
ክብሬ ማንነቴ ነሽ እናቴ
ጀምሬም ባልጨርሰው
ስምሽን ላወድሰው
ገነት ላንቺ ለምድሯ
ሳመሰግን ለ አምላክ ስራ
እድሜ ሰቶ እንዲያሳይሽ
ታናሽ ታላቅ እንደህልምሽ ሲሆንልሽ
ያ ምርቃት የማልረሳው
ልቤን ሲወድቅ የሚያነሳው
አደረሰኝ ከ ደጃፉ
በፀሎትሽ ከ ፅሁፉ
ታሪክ
Written by: Kirubel Bacha, SAMUEL TEFERI
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...