album cover
Habte
2,447
World
Habte was released on March 22, 2023 by Zeritu Kebede as a part of the album Atihidibign
album cover
Release DateMarch 22, 2023
LabelZeritu Kebede
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM120

Credits

PERFORMING ARTISTS
Zeritu Kebede
Zeritu Kebede
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Zeritu Kebede
Zeritu Kebede
Songwriter

Lyrics

የምወደው ነገር ሁሉ ተደራርቦ
በሱ ሊታይ ቻለ አንድ ላይ ተክቦ
ደስ የሚል ፀጋ እሱን ማረግ የራስ
በእቅፉ መሸለብ ደረቱን መንተራስ
ከናፍር ተዋደው በፍቅር ሲቀሉ
እንጆሪ ሲመስሉ ጣፋጭ የሚበሉ
እንዴት ያስደስታል ከሱ ጋር መጫወት
ሊመስለኝ አልቻለም ህልም እንጂ የ'ውነት
ሰው ባለው ይኮራል እኔም በሱ በሃብቴ
ያለኝ ጌጥ እሱ ነው መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም አይሸጥ አይለወጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
በፀጉሩ መሀከል ጣቶቼን ማንሸርሸር
በቀልድ በጨዋታ በፈገግታው መስከር
በፍቅር አፍዞኝ አይኑን ስመለከት
የጠገብኩ መሰለኝ የገባሁኝ ገነት
በፍቅር ላይ ፍቅር እየጨማመረ
ሀብቴ ተትረፍርፎ በልቤ ከበረ
ይሄ ሁሉ ደስታ ይሄ ሁሉ ሀሴት
ሊመስለኝ አልቻለም ህልም እንጂ የእውነት
ሰው ባለው ይኮራል እኔም በሱ በሃብቴ
ያለኝ ጌጥ እሱ ነው መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም አይሸጥ አይለወጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
ፍቅር ይስጥሽ ብሎ ማነው የመረቀኝ
ይህን የመሰለ መልአክ የገጠመኝ
ሀብቴ መዋቢያዬ ጌጤ ብዬዋለው
ፍቅሬ ቅርስ ሆኖኛል እኔ ወደዋለው
ሰው ባለው ይኮራል እኔም በሱ በሃብቴ
ያለኝ ጌጥ እሱ ነው መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም አይሸጥ አይለወጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
ሰው ባለው ይኮራል እኔም በሱ በሃብቴ
ያለኝ ጌጥ እሱ ነው መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም አይሸጥ አይለወጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
ሰው ባለው ይኮራል እኔም በሱ በሃብቴ
ያለኝ ጌጥ እሱ ነው መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም አይሸጥ አይለወጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
ለኔ ግን የት አለ ከሱ የሚበልጥ
Written by: Zeritu Kebede
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...