album cover
Sint New?
album cover
Sint New? was released on January 14, 2024 by YEMa as a part of the album Yedega Sew
January 14, 2024
LabelYEMa
BPM138
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ
ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ (ልኬ ሆኗል እሱ)
ስወድህ ውደደኝ እንካ ፍቅር ባቅሜ
ማርኮ ይግዛኝ ልብህ አጠይቀኝ እድሜ
አፌ ቃል ቢያወጣም አይሰማም ድምጼ
ስንት ነው? አትበለኝ ካልነገረህ ገጼ
ስንት ነው? ሰንት ያየውን
አይገልጸው ፍቅር ጸቡን
መውደድህ ካልሆነኝ መርኪያ
ስንት ነው? እድሜ መለኪያ
ለፍቅር ያልታጨ ለመውደድ ያልታጨ
እልፍ ዓመት ቢኖርም ባጭር የተቀጨ
ለፍቅር ያልታጨ ለመውደድ ያልታጨ
እልፍ ዓመት ቢኖርም ባጭር የተቀጨ
ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ
ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ
ዘላለም ናት ዛሬ ከምወድህ ጋራ
ቁጥር ያለ ፍቅር ቢከምሩት ተራ
የጊዜ መለኪያ እርዝመት እጥረቱ
ፍቅር ናደው እንጂ እኩል ነው ሰዓቱ
ስንት ነው? ስንት ያየውን
አይገልፀው ፍቅር ፀቡን
መውደድህ ካልሆነኝ መርኪያ
ስንት ነው እድሜ መለኪያ
ለፍቅር ያልታጨ ለመውደድ ያልታጨ
እልፍ ዓመት ቢኖርም ባጭር የተቀጨ
ለፍቅር ያልታጨ ለመውደድ ያልታጨ
እልፍ ዓመት ቢኖርም ባጭር የተቀጨ
እህህህ
እህህህ
ተድላ ሙሉ ዓመታት ስንኖር ተፋቅረን
እንደተቃቀፍን አብረን እንቆጥራለን
አንድ ይባል እድሜያችን ፍቅር መቃመሱ
እንቁጠር ይንጋና ይጀመር ካ'ዲሱ
ስንት ነው ሰንት ያየውን
አይገልጸው ፍቅር ጸቡን
መውደድህ ካልሆነኝ መርኪያ
ስንት ነው እድሜ መለኪያ
ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ
ይጀመር ካ'ዲሱ ይቆጠር ካ'ዲሱ
የዕድሜዬ መነሻ ልኬ ሆኗል እሱ
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...