album cover
Sabegn
327
Christian & Gospel
Sabegn was released on September 3, 2024 by Selam Desta as a part of the album Sabegn - Single
album cover
Release DateSeptember 3, 2024
LabelSelam Desta
LanguageEnglish
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM76

Music Video

Music Video

Credits

PERFORMING ARTISTS
Selam Desta
Selam Desta
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Selam Desta
Selam Desta
Songwriter

Lyrics

ና ብለህ የጠራኸው ወደ ዕልፍኝ ያስገባኸው
የእውነትን እውቀት ካንተ የቀዳ ሰው
ከውጭ ብርድ ያመልጣል ፍቅርህ ያሞቀዋል
አንዱ ብዙ ሆነ ሁሉን አስንቀሃል
ረቢ ሆይ ከወዴት ትኖራለህ
ውዴ ሆይ ወዴት ታሰማራለህ
ሁሉን ጥዬ እንድከተልህ
ሳበኝ ልሩጥ ከኁላህ
ከደረቅ መሬት እንደ ስር የበቀልክ የቆላ አበባ
ፅድቅን እንዳገኝ የታረድክልኝ በዚያ በኮረብታ
አይኔን አልነቅልም ከተከልኩበት ከመስቀልህ ላይ
መስቀሌን ይዤ እከተልሃለሁ ሳበኝ እላለሁ
ረቢ ሆይ ከወዴት ትኖራለህ
ውዴ ሆይ ወዴት ታሰማራለህ
ሁሉን ጥዬ እንድከተልህ
ሳበኝ ልሩጥ ከኁላህ
ለጥቂት ግጦሽ እንዳልቀላውጥ መሰማሪያ ለምለም መስኬ ነህ
ከያዕቆብ ጉድጓድ ትባልጣለህ የዘላለም ውሃ ምንጭ ነህ
ለአንዴና ለሁሌ የምትሆን ፋሲካዬ ነህ
አንተ ያለህበት የነፍሴ በዓል ነው ሳበኝ እላለሁ
ረቢ ሆይ ከወዴት ትኖራለህ
ውዴ ሆይ ወዴት ታሰማራለህ
ሁሉን ጥዬ እንድከተልህ
ሳበኝ ልሩጥ ከኁላህ
የደከምሁ ቀን ባንተ እንድበረታ እንዳልረታ
ከወደቅሁበት በኃይልህ ችሎት ፈጥኜ እንድነሳ
በከፍታዎች መብረር እድችል እንዳያቅተኝ
አለቴ ሆይ ወዳንተ እሸሻለሁ ሳበኝ እላለሁ
ረቢ ሆይ ከወዴት ትኖራለህ
ውዴ ሆይ ወዴት ታሰማራለህ
ሁሉን ጥዬ እንድከተልህ
ሳበኝ ልሩጥ ከኁላህ
Written by: Selam Desta
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...