album cover
Fera Firhate
617
Christian & Gospel
Fera Firhate was released on October 4, 2024 by Aster Abebe as a part of the album Hallelujah
album cover
Release DateOctober 4, 2024
LabelAster Abebe
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM111

Music Video

Music Video

Credits

PERFORMING ARTISTS
Aster Abebe
Aster Abebe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Aster Abebe
Aster Abebe
Songwriter

Lyrics

ፈራ ፍርሃቴ
ደረበልኝ በላይ አለበሰኝ ጸጋ
እንዲሆነኝ አቅም እስክደርስ እርሱ ጋ
በአቅመኞች ጉልበት በብርቱዎች ማደም
የማትገፈፍ ልብሴ ለኔ እንዳንተ የለም
ደረበልኝ በላይ አለበሰኝ ጸጋ
እንዲሆነኝ አቅም እስክደርስ እሱ ጋ
በአቅመኞች ጉልበት በብርቱዎች ማደም
የማትገፈፍ ልብሴ ለኔ እንዳንተ የለም
1- በህብሮች ቀለም በተንቆጠቆጠች
ከወንድሞች መሃል ለዮሴፍ ለተባለች
ቢውልባት ደምቆ ለብሶ ቢያምርበት
ቢያሳብቅ ሞገሱን አይንህ እንዳረፈበት
ዛቻ ሲጠብቀው መልካም እያሰበ
እንጀራ አቀብሎ ጉድጓድ ለተቸረ
ለሰው ሃገር ሰዉ ጠብቀህ ዘመንን
በአንተው እጅ ለበሰ የማይገፈፈውን
2- የንጉስ ልብ ከፍቶ ጦርን ሲወረውር
የተቀባው ቅባት ሲያስነሳ ስደትን
በእባብ ጊንጥ መኖሪያ በአዶላም ዋሻ
ስንቱን አስጀገነ ሆነኸው ድል መንሻ
መጠጊያ ለሌለው ማስገቢያ ለአንገቱ
ስንቱ ተማምኖብህ ተረፈ ለስንቱ
ሸለቆው ጠገበ በጠልህ ረስርሶ
ቀን እስኪወጣለት አንተን ተንተርሶ
ፈራ ፍርሃቴ ቃልህን ስትናገር
ሸሸ ጨለማዬ ነጋ በእኔ መንደር
ጥንካሬ አገኘኝ ፊትህን በማየት
ደመቀ ህይወቴ ከአንተ በመቆየት
ፈራ ፍርሃቴ ቃልህን ስትናገር
ሸሸ ጨለማዬ ነጋ በኔ መንደር
ጥንካሬ አገኘኝ ፊትህን በማየት
ደመቀ ህይወቴ ከአንተ በመቆየት
ከላይ ከውሽንፍር ጥላ ከሃሩሩ
የጸናልኝ ቤቴ መርከብ በማዕበሉ
የማይደፈር አጥር ለጎመጀኝ አውሬ
ትልቁን ወግድ ባይ የማይነቀነቅ በሬ
ከላይ ከውሽንፍር ጥላ ከሃሩሩ
የጸናልኝ ቤቴ መርከብ በማዕበሉ
የማይደፈር አጥር ለጎመጀኝ አውሬ
ትልቁን ወግድ ባይ የማይነቀነቅ በሬ
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው አዎ
ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ
መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ
ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ
መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ
ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው
ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው
ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው
ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው አዎ
አዎ ስምህ ነው
Written by: Aster Abebe
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...