album cover
Kunjina
album cover
Kunjina was released on June 9, 1999 by Dawit Mellesse as a part of the album Anchin New
June 9, 1999
LabelDawit Mellesse
LanguageEnglish
BPM50
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ
ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ
መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ
ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ
አለተፈጠረም ሰው የለሽም አምሳያ
የቁንጅና ጣርያ የውበት ማሰሪያ
በሰፈሩ ሁሉ የሚያማምር ሞልቶ
ውበትሽ እንደ አርማ የሚታየው ጎልቶ
የንግስት ግርማ አለሽ አንገት የሚያስደፋ
ቃልሽ ምስክር ነው እውነት እንዳልጠፋ
ቢፈጠር ርቀት ከሰማይ ሰማይ
እመጣ ነበር አይንሽን እንዳይ
መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ
ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ
መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ
ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ
ዝልፍልፍ ነው ፀጉርሽ እንዳሻው ተኝቷል
ወገብሽን እንዳላይ ደብቆ ይዞታል
ዳሌሽም ተስማምቶ በምቾት ተቀምጧል
ሽንጥሽ ለእጄት ያክል ለመያዣ ቀርቷል
ጨረቃም አትውጣ ፀሀይም ትጥለቅ
ጥርስሽ ላገር በቂ የሚያንፀባርቅ
ኮኮቦች በላይሽ ከበው ያወራሉ
ውበትሽ ማርኳቸው ዙርያሽን ያያሉ
ጌጣጌጥሽን ጣይው ኩሉስ ለምንሽ
እንከን ሳይወጣለት ተፈጥሮ ገላሽ
መቀነትሽን ፍቺው ምን አንጀት አለሽ
እባብ እና ነበር ቀንተው እያዩሽ
አይንሽም ቅዱስ ነው ክፋት እንዳያይ
ተረከዝሽ እንቡጥ ችሎ አቆመሽ ወይ
ጠረንሽ የአበባ ንብን ያሳስታል
ውበትሽ ለግላጋ ሰውን ያስገምታል
Written by: Dawit Mellesse
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...