album cover
Menelik
561
World
Menelik was released on January 1, 2003 by AIT Records, Inc. as a part of the album Menelik
album cover
AlbumMenelik
Release DateJanuary 1, 2003
LabelAIT Records, Inc.
LanguageEnglish
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM106

Credits

Lyrics

ብወጣው በእግሬ እንጦጦን
አላገኝም ወይ ጣይቱን
ፍቅሩን አብዝቶት ያለልክ
ዛሬም ይባላል ምኒልክ
አሆይ ይወራል ዘንድሮ
ያበላ በድሮ
እስኪ ወደ አንኮበር ተነሱ እንዝለቀው
እኛ አናየውም ወይ ምኒልክ ቢለቀው
የጣይቱን ማጀት ቢፈልጉት እዛ
አይጠፋም እስካሁን የጠጇ መዓዛ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
ከእልፍኝ ካዳራሹ በአካል ባናገኘው
የግብሯ ትዝታ ዛሬም ከግቢው ነው
ሙያዋ ቢጣፍጥ የዛች የእመቤት
ተበላ ተጠጣ በምንሊክ ቤት
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አሆሆይ
ብወጣው በእግሬ እንጦጦን
አላገኝም ወይ ጣይቱን
ፍቅሩን አብዝቶት ያለልክ
ዛሬም ይባላል ምኒልክ
አሆይ ይወራል ዘንድሮ
ያበላ በድሮ
እስኪ አንተ ሸውዬ እንዳባትህ ስራ
ከጓዳ እንድንቀዳው ወተቱን በእንስራ
ደግነትክን ሳላይ በዋልክበት ውዬ
ደርሶ እንደ ምኒልክ አልልክ እምዬ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
ያገኘክ እንደሆን ግቢን ከአዲሳባ
የደግ አዳራሽ ነው ሰተት ብለህ ግባ
አይቆረቁረውም እንግዳ ደጁን
ገብቶ ይጥገብ እንጂ ስጋና ጠጁን
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አሆሆሆ
ብወጣው በእግሬ እንጦጦን
አላገኝም ወይ ጣይቱን
ፍቅሩን አብዝቶት ያለልክ
ዛሬም ይባላል ምኒልክ
አሆይ ይወራል ዘንድሮ
ያበላ በድሮ
ያ ሁሉ ደስታ ፊቴ ይደቀናል
ሰው እንዴት በሄደው ባለፈው ይቀናል
ያ የፍቅር ጊዜ ያ ደስታ ቀን
ደግሞ በዓይኔ መጣ ከፊቴ ሊደቀን
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አጀብ ጉዳዴ
አሆሆሆ
ደግሞ ደግሞ
ደግሞ ደግሞ
ደግሞ ደግሞ
አሆሆሆ
Written by: Rahel Yohannes, Surafel Abebe, Yilma Gebre-ab
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...